በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መርዛማ እባብ ጀርባው ላይ የወጣበት አብራሪ አውሮፕላኑን ካለ ችግር አሳረፈ

መርዛማ እባብ ጀርባው ላይ የወጣበት አብራሪ አውሮፕላኑን ካለ ችግር አሳረፈ
መርዛማ እባብ ጀርባው ላይ የወጣበት አብራሪ አውሮፕላኑን ካለ ችግር አሳረፈ

አንድ ደቡብ አፍሪካዊ አውሮፕላን አብራሪ አደገኛ እባብ ጀርባው ላይ ከወጣ በኋላ አውሮፕላኑን ካለ ችግር በማሳርፉ አድናቆት ተችሮታል።

አራት ሰዎችን ጭኖ አንዲት አነስተኛ የግል አውሮፕላን ሲያበር የነበረው ሩዶልፍ ኢራስመስ ወደ ፕሪቶሪያ በማቅናት ላይ ሳለ፣ አደገኛና ገዳይ መርዝ እንዳለው የሚታወቀው ኬፕ ኮብራ የተሰኘው የእባብ ዓይነት በጀርባው ላይ ሲሄድ ተሰምቶታል።

የእባቡ ዓይነት በአብዛኛው በደቡብ አፍሪካ የሚገኝና መድሃኒት ካላገኙ መርዙ ገዳይ መሆኑን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

ቀዝቀዝ ያለ ነገር ጀርባውን ሲጫነው እባቡ እንደወጣበት ማወቁን ኢራስመስ ተናግሯል።

የአገሪቱ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ለአብራሪው አድናቆቱን ገልጿል።

XS
SM
MD
LG