በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ አፍሪካው ራማፎሳ ለሁለተኛ ጊዜ የፕሬዝዳንትነት ቃለ መሃላ ፈጸሙ


የደቡብ አፍሪካው ራማፎሳ ለሁለተኛ ጊዜ የፕሬዝዳንትነት ቃለ መሃላ ፈጸሙ
የደቡብ አፍሪካው ራማፎሳ ለሁለተኛ ጊዜ የፕሬዝዳንትነት ቃለ መሃላ ፈጸሙ

የደቡብ አፍሪካው መሪ ሲሪል ራማፎሳ ለሁለተኛ ግዜ የፕሬዝዳንትነት ቃለ መሃላ በመፈጸም አዲስ የስልጣን ዘመን ጀምረዋል። ራማፎሳ ስልጣኑን በድጋሚ የተረከቡት የተዳከመው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲያቸው በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያስችለውን የመንግስት ጥምረት ስምምነት በከፍተኛ ጥረት ከተቀዳጀ በኃላ ነው።

በግንቦት መጨረሻ በተካሄደው የደቡብ አፍሪካ አጠቃላይ ምርጫ በሦስት አስርት አመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ምንም አይነት አሸናፊ ሳይኖር ቢቀርም፣ የሕግ አውጪዎች ባለፈው ሳምንት የ71 አመቱን አዛውንት በድጋሚ መርጠዋቸዋል።

በፕሪቶሪያ ውስጥ የመንግስት መቀመጫ በሆነው አንድነት ህንፃ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ቃለ መሃላ የፈፀሙት ራማፎሳ ባደረጉት ንግግር "የብሔራዊ አንድነት መንግስት ምስረታ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው የአዲስ ዘመን መጀመሪያ ነው" ያሉ ሲሆን፣ "የደቡብ አፍሪካ መራጮች ሀገራችንን አንድ ፓርቲ በብቸኝነት እንዲያስተዳድረው ሙሉ ስልጣን አልሰጡም" ሲሉ አክለዋል።"

ራማፎሳ በህግ አውጪዎች፣ የውጭ ሀገር መሪዎች፣ የሀይማኖት እና የባህል መሪዎች እና ደጋፊዎች ፊት ባደረጉት በዚሁ ንግግር ሕዝቡ "ችግራቸውን ለመፍታት እና ምኞታቸውን እውን ለማድረግ በጋራ እንድንሰራ መመሪያ ሰጥተውናል" ሲሉም ተናግረዋል።

ፓርቲያቸው ከጥምረቱ አባላት ጋር ድርድር በቀጠለበት ወቅት፣ ራማፎሳ በመጪዎቹ ቀናት የካቢኔ አባላቶቻቸውን ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቃለ መሃላ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የናይጄሪያውን ፕሬዝዳንት ቦላ አህመድ ቲኑቡ፣ የአንጎላውን ዡዋ ሎራንሶ፣ የኮንጎ ብራዛቪሉን ዴኒስ ሳሱ ንጉዌሶን እና የኢስዋቲኒን ንጉስ ምስዋቲ ሦስተኛ ጨምሮ በርካታ የሀገር መሪዎች ተገኝተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG