በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ራማፎሳ ከተደረገባቸው የገንዘብ ቅሌት ምርመራ ነጻ ሆኑ


የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ፤ በገጠር መኖሪያ ቤታቸው በሚገኝ ሶፋ ውስጥ ተቀምጦ የነበረና፣ በኋላም በዘራፊዎች ተወስዷል ከተባለ ገንዘብ ጋር በተያያዘ፣ በአገሪቱ የሙስና ኮሚሽን ሲደርግባቸው የነበረው ምርመራ ተጠናቆ፣ ፕሬዝደንቱ የጣሱት ሕግ እንደሌለ ተገልጿል።

ጉዳዩ ይፋ የሆነው ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ሲሆን፣ ከሶስት ዓመት በፊት በፕሬዝደንቱ የገጠር ቤት ላይ በተፈጸመ ዝርፊያ፣ ጥሬ የውጪ አገር ገንዘብም መሠረቁን ፕሬዝደንቱ ሪፖርት አላደረጉም ሲል አንድ የቀድሞ የአገሪቱ የስለላ ተቋም ሃላፊ መጠቆማቸውን ተከትሎ ነው።

ፕሬዝደንቱ እና ፓርቲያቸው ጥፋተኛ አለመሆናቸውን በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል። ገንዘቡም ለአንድ ሱዳናዊ ነጋዴ ጎሾችን ሸጠው ያገኙት 580 ሺህ ዶላር እንደሆነ ተናግረዋል።

ራማፎሳ ስርቆት መፈጸሙን ለፖሊስ ሪፕርት ከማድረግ ይልቅ፣ ዘራፊዎቹ እንዲታፈኑ አድርገዋል፣ ገንዘቡም መንግስት የማያውቀው ነው በሚል ክስ ሲቀርብባቸው ቆይቷል።

የአገሪቱ ኦምቡድስማን ቢሮ ዛሬ በለቀቀው የምርመራ ውጤት፣ ፕሬዝደንቱ ቤት ገንዘብ በመገኘቱ ራማፎሳ የጣሱት ሕግ አለመኖሩን እና ስርቆት መፈጸሙንም በማግስቱ ለፖሊስ ሪፖርት አድርገዋል ብሏል።

XS
SM
MD
LG