በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ አፈ ጉባኤ በሙስና ተከሰሱ


ፎት ፋይል፦ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ኖሲቪው ማፒሳ ንቃኩላ፣ በፕሪቶሪያ ፍርድ ቤት
ፎት ፋይል፦ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ኖሲቪው ማፒሳ ንቃኩላ፣ በፕሪቶሪያ ፍርድ ቤት

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ አፈ ጉባኤ በሙስና እና በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ በማድረግ ተከሰዋል።

ክሱ የገዢው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) በመጪው ወር በሚደረገው ምርጫ በሚያደርገው ተሳትፎ ላይ ጥላ ያጠላል ተብሏል።

ትናንት ከአፈ ጉባኤ ወንበራቸው የተነሱት ኖሲቪው ማፒሳ ንቃኩላ፣ እራሳቸውን ለፖሊስ በማቅረብ ዛሬ ፕሪቶሪያ ውስጥ በሚገኝ ፍ/ቤት ቀርበዋል። አስራ ሁለት የሚሆኑ የሙስና ክሶች አንዲሁም በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ በማድረግ አንድ ክስ ቀርቦባቸዋል።

የ67 ዓመቷ አፈ ጉባኤና የኤኤንሲ የረጅም ግዜ ዓባል በዋስ እንዲለቀቁ ፍ/ቤት እንደወሰነላቸው የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

የአፈ ጉባኤዋ ክስ በደካማ ኢኮኖሚ እና ሙስና ምክንያት የሕዝብ ድጋፉን እያጣ ላለው ኤኤንሲ ተጨማሪ ችግር ነው ተብሏል። የኤኤንሲ አመራሮች፣ ፕሬዚዳንት ሰሪል ራማፎሳ እና ምክትላቸውን ጨምሮ የሙስና ክስ ተመሥርቶባቸዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG