በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ አፍሪካ ወታደሮቿን ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ አስወጣች


ኪንሻሳ፣ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ
ኪንሻሳ፣ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ

ደቡብ አፍሪካ 127 የሚኾኑ ወታደሮቿን ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ አስወጥታለች፡፡ አራቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው መኾኑም ታውቋል።

ወታደሮቹ ከሁለት ዓመታት በፊት የ16 ሀገራት ጥምር በሆነው በደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ ወይም ሳድክ ኅይል ውስጥ ታቅፈው፣ በሩዋንዳ ከሚደገፈው ኤም 23 ጋራ በመፋለም ላይ ያለውን የኮንጎ መንግሥት ለመደገፍ የተሠማሩ ነበሩ።

ሃያ አንዱ ወታደሮች ትላንት ማክሰኞ የተመለሱ ሲሆን፣ 106 የሚሆኑት ደግሞ ዛሬ ረቡዕ ተመልሰው ደቡብ አፍሪካ ወታደሮቿን በሙሉ አስወጥታ አጠናቃለች፡፡

የተጎዱት ወታደሮች ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ፣ ከተመለሱት ውስጥ አንዳንዶቹ የሥነ ልቦና ሕክምና እንደሚያስፈልጋቸውም ታውቋል።

የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ባለፈው ጥር የተገደሉ 14 ወታደሮችን አስከሬን እንድታስመልስ በሃገሪቱ ውስጥ ጫና በርትቶበት ነበር።

ደቡብ አፍሪካ በአጠቃላይ አንድ ሺሕ የሚሆኑ ወታደሮችን ወደ ኮንጎ እንዳሰማራች ሪፖርቶችና ትንተናዎች ቢያመለከቱም፣ ባለሥልታናት ግን ትክክለኛውን ቁጥር አልገለጹም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG