ገዥው የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ (ኤኤንሲ) የአፓርታይድ ስርዓት ካበቃበት ከዛሬ 30 ዓመታት ወዲህ ለዚያች ሃገር የመጀመሪያ የሆነውን ጥምር መንግስት ለመመስረት ከዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሕብረት ፓርቲ (ዲኤ) ጋራ በዛሬው ዕለት ከስምምነት ላይ ደርሷል።
ስምምነቱ የኤኤንሲው መሪ ሲሪል ራማፎሳ በፕሬዝዳንትነት ሥልጣናቸው እንዲቀጥሉ ቢያስችልም፤ የኢኤንሲ የ30 ዓመት የሥልጣን የበላይነት ማብቂያ ምልክት ሆኗል።
ባለፈው ግንቦት 21 በተካሄደው ምርጫ ከአጠቃላዩ የመራጭ ድምጽ 40 በመቶውን ብቻ በማግኘት በሃገሪቱ ፓርላማ የነበረውን አብላጫ ድምጽ ያጣ ሲሆን፤ የመሃል ቀኝ ዘመሙ የዲኤ ፓርቲ 21 በመቶውን ድምጽ አግኝቷል።
ከዚህ በተጨማሪም ሁለቱ አናሳ ፓርቲዎች፣ የማህበራዊ ወግ አጥባቂው ኢንካታ የነፃነት ፓርቲ እና ቀኝ ዘመሙ የአርበኞች ህብረት የአዲሱ መንግስት አካል ይሆናሉ ተብሏል።
መድረክ / ፎረም