በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፕሪቶሪያ በተመድ ቢሮ ደጃፍ ላይ ተጠልለው የነበሩ ስደተኞችን ፖሊስ አስነሳ


ፎቶ ፋይል፦ የተመድ ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ቢሮ ደጃፍ ላይ ተጠልለው የነበሩ ጥገኝነት ጠያቂዎችን የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሲስነሳ እአአ 2019
ፎቶ ፋይል፦ የተመድ ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ቢሮ ደጃፍ ላይ ተጠልለው የነበሩ ጥገኝነት ጠያቂዎችን የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሲስነሳ እአአ 2019

ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑና በፕሪቶሪያ የተመድ ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ቢሮ ደጃፍ ላይ ተጠልለው የነበሩ ጥገኝነት ጠያቂዎችን የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እንዲነሱ አድርጓል።

መጤዎች በሚሏቸው ላይ የአገሪቱ ዜጎች በሚያደርሱት ጥቃት ምክንያት ስደተኞቹ ወደ ሌሎች አገሮች ተላልፈው እንዲሰጡ በመጠየቅ ላለፉት ሦስት ዓመታት በስደተኞች ኮሚሽኑ ቢሮ ደጃፍ ላይ ጊዜያዊ መጠለያ ሰርተው ኖረዋል።

የፕሪቶሪያ ማዘጋጃ ቤት ባለፈው ሳምንት ስደተኞቹን ለማንሳት የፍርድ ቤት ፈቃድ ማግኘቱን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል። ስደተኞቹ ካለፈቃድ ወደ አገር ውስጥ የገቡ ሰዎች የሚቆዩበት ማዕከል ተወስደው፣ ከዛም ወደ መጡበት አገር እንደሚመልሱ ታውቋል።

አንዳንድ ቤተሰቦች በፈቃዳቸው ሲነሱ፣ ሌሎች ደግሞ ተቃውሞ አድርገዋል።

“ወደ ሌላ አገር እንድናዛውራቸው ጠይቀውናል፣ ነገር ግን ያንን ማድረግ የእኛ ሥራ አይደለም” ሲሉ የተመድ ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ሎራ ፓዶዋን መናገራቸውን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG