በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎች ተስማሙ


ፎቶ ፋይል፦ ሳልቫኪር እና ሪክ ማቻር
ፎቶ ፋይል፦ ሳልቫኪር እና ሪክ ማቻር

ተፋላሚዎችና ባላንጣዎች የሆኑት የደቡብ ሱዳን መሪዎች በጎረቤት አገር ሱዳን በተደረገ ሽምልግና ትልቅ እመርታ ነው ከተባለለት ሥምምነት መድረሳቸው ተነገረ፡፡

በደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪርና ተቀናቃኛቸው ም/ፕሬዚዳንት ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር እኤአ የ2018 ለተደረሰበት ሥምምነት መሰናክል ሆኖ የቆየውንና አገሪቱን ለአምስት ዓመታት በእርስ በርስ ጦርነት ስር እንድትዳክር ያደረጋትን ቁልፍ ጉዳይ የሚያስወግድ ሥምምነት ነው ተብሏል፡፡

ሥምምነቱ የሁለቱን ወገኖች ሠራዊት በማዋሃድ በአንድ ዕዝ ሥር እንዲሆኑ ማዋቀርን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ጉዳዮችንም ያካተተ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የማቻር ፓርቲ ወክለው ስምምነቱን የፈረሙት ማርቲን አቡቻ ሰላም ማለት ደህንነትን ማረጋገጥ ነው ዛሬ እሱን ለማረጋገጥ የመሠረት ድንጋይ ጥለናል ብለዋል፡፡

የፕሬዚዳንት ክሪር የፀጥታ አማካሪ የሆኑት ቱት ጋትላክ በበኩላቸው ይህ እኛ ለሰላም መቆማችንን ያሳያል አሁን ሁላችንም ለሰላም እንስራ” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG