በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ኮሪያ፣ ዩናይትድ ስቴትስና ጃፓን ፀረ ባህር ሰርጓጅ ልምምድ አደረጉ

US aircraft carrier USS Ronald Reagan, top right, participates with other US and South Korean navy ships during the joint naval exercises between the United States and South Korea in waters off South Korea's eastern coast in South Korea, on Sept. 29, 2022

የደቡብ ኮሪያ፣ የዩናይትድ ስቴትስና የጃፓን የጦር መርከቦች፣ ከአምስት ዓመት በኋላ የመጀመሪያቸው የሆነውን የጋራ ጸረ ባህር ሰርጓጅ ልምምድ ማድረጋቸው ተነገረ፡፡

ሦስቱ ሀገሮች ልምምዱን ያደረጉት ደቡብ ኮሪያና የዩናይትድ ስቴትስ በጋራ ልምምድ ማድረጋቸውን ተከትሎ በዚህ ሳምንት የሚሳይል ሙከራዎችን እንደገና ለቀጠለችው ለስሜን ኮሪያ ምላሽ ለመስጠት መሆኑን የአሶሴየትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ሰሜን ኮሪያ በአንድ ወር ውስጥ በዚያ መጠን ሲካሄዱ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የተነገረላቸውን የቅርብ ጊዜዎቹን አምስት የሚሳይል ሙከራዎች ያካሄደችው የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ ደቡብ ኮሪያን ከመጉብኘታቸውን በፊትና በኋላ መሆኑ ተዘገቧል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንት ትናንት ሀሙስ ባሰሙት ንግግር ዩናይትድ ስቴትስ የእስያ አጋሮችዋን ደህንነት መጠበቅ “እንደብረት የጠነከረ ነው” ያሉትን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡

በኮሪያ ምስራቃዊ የባህር ወሽመጥ ለአንድ ቀን የተካሄደው የሦስቱ አገሮች የባህር ላይ ልምምድ፣ ሰሜን ኮሪያ ከባህር ሰርጓጅ መርከቦች የምታስወነጭፈውን ሚሳኤል መመከት የሚያስችለውን ብቃት ለማጎልበት መሆኑን የደቡብ ኮሪያ ባህር ኃይል ያወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG