በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩዋንዳ ወታደራዊ ኃይል የኮንጎ ስደተኞች ላይ ተኩስ ከፈተ


የሩዋንዳ ወታደራዊ ኃይል መጥፎ የኑሮ ሁኔታን በመቃወም ከመጠለያቸው በወጡት የኮንጎ ስደተኞች ላይ ዛሬ ተኩስ ከፍቷል።

የሩዋንዳ ወታደራዊ ኃይል መጥፎ የኑሮ ሁኔታን በመቃወም ከመጠለያቸው በወጡት የኮንጎ ስደተኞች ላይ ዛሬ ተኩስ ከፍቷል።

ከሦስት እስከ አስር ሺህ የሚሆኑ ስደተኞች በምዕራብ ሩዋንዳ ካሮንጊ ወረዳ ላይ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰደተኞች አገልግሎት መሠሪያ ቤት ፊት ተቃውሞ ለማካሄድ ሲሉ ኪዚባ ካለው መጠለያችቸው ወጥተው ለሁለት ሰዓታት በእግር ተጉዘዋል።

በአሜሪካ ድምፅ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፖብሊክ አገልግሎት ዘጋቢ በዘገበው መሰረት ወታደርዊው ኃይል በከፈተባቸው ተኩስ አንድ ስደተኛ ቀላል ጉዳት ደርሶበታል።

ስደተኞቹ ወደ ሌላ ሀገር ሄደው ለመስፈር ነው የሚፈልጉት። ካልሆነ ግን ወደ ሀገራቸው በእግር እንደሚመለሱ ገልፀዋል።

“በመብታችን ችላ መባል ተሰላችተናል። እዚህ ደኅንነት አይሰማንም። እዚህ አገር ሀገር መኖር ስለማንችል ወደ ሌላ ሀገር ሄደን ለመስፈር እንፈልጋለን” ሲሉ በኪዚባ ካምፕ ያለው የኮንጎ ስደተኞች ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ሉዊስ ማኦምቢ አስገንዝበዋል።

ኪዚባ በሀገሪቱ ከቆዩት የስደተኞች ሰፈሮች አንዱ ሲሆን 17,000 የሚሆኑ የኮንጎ ተወላጆች ተጠለውበታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG