በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሩዋንዳ የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 130 ደረሰ

በሩዋንዳ ሰሞኑን የጣለው ከባድ ዝናም ባስከተለው ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት፣ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 130 መድረሱ ታውቋል።
በሩዋንዳ ሰሞኑን የጣለው ከባድ ዝናም ባስከተለው ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት፣ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 130 መድረሱ ታውቋል።

በሩዋንዳ ሰሞኑን የጣለው ከባድ ዝናም ባስከተለው ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት፣ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 130 መድረሱ ታውቋል።

ተራራማ በኾነችው ሩዋንዳ፣ ከብዙ ዓመታት በኋላ የደረሰ ነው በተባለው አደጋ፣ በሺሕ የሚቆጠሩ ዜጎች ያለመኖሪያ ቤት ቀርተዋል።

የኪቩ ሐይቅ የሚገኝበት ምዕራባዊ አውራጃ በተለይ፣ ከፍተኛ አደጋ እንደደረሰበት ታውቋል። በመሬት መንሸራተቱ የተፈጠረው የጭቃ ጎርፍ፣ ቤቶችን ሲያወድም እና መንገዶችን ሲዘጋ ሌሎች መሠረተ ልማቶችንም አውድሟል።

“ልጄን ድንጋይ እና አለት ውስጥ ተቀብሮ አገኘኹት። ሆስፒታል ስንደርስ ሕይወቱ አለፈ፤” ስትል አኖንሲያታ የተባለች ወላጅ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግራለች። “ለቤተሰቤ ከባድ ወቅት ነው። ሌላው ልጄም ጭንቅላቱ ክፉኛ ተጎድቷል፤ ይተርፋል ብዬ ተስፋ አደርጋለኹ፤” ስትል አክላለች።

አንድ አባት እና ባለቤቱ፥ ልጆቻቸውን ሲጣሩ ቢውሉም እንዳልመለሱላቸውና ከቆይታ በኋላ ሁሉም ሞተው እንዳገኟቸው፣ ለኤኤፍፒ ተናግረዋል።

5ሺሕ100 የሚኾኑ ቤቶች፣ በአደጋው መውደማቸውንና 2ሺሕ500 የሚኾኑቱ ደግሞ ጉዳት እንደ ደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል።

XS
SM
MD
LG