በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያው ፕሬዝደንት አሜሪካንን ሊጎበኙ ነው


የኬንያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ
የኬንያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ

የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ በመጪው ሐሙስ በአሜሪካ ጉብኝት በማድረግ፣ ከፕሬዝደንት ጆ ባይደን ጋራ እንደሚገናኙ ታውቋል።

በሄይቲ ያለው ቀውስና በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት የንግግራቸው ዋና አጀንዳ እንደሚሆን ይጠበቃል።

በሩቶ ቢሮ “ታሪካዊ” በሚል የተገለጸው ጉብኝት፣ በአንድ የኬንያ መሪ ሲደረግ ከሃያ ዓመታት በኋላ ሲሆን፣ በአንድ አፍሪካዊ መሪ በአሜሪካ ኦፊሴላዊ ጉብኝት ሲደረግ ደግሞ ከእ.አ.አ 2008 ወዲህ የመጀመሪያው መሆኑ ነው። በ 2008 አሜሪካንን በይፋ የጎበኙት አፍሪካዊ መሪ የጋናው ፕሬዝደንት ጆን ኩፎር ነበሩ።

ሩቶ ሐሙስ ከጆ ባይደን ጋራ በሚኖራቸው ውይይት፣ ሄይቲ የገጠማትን ቀውስ ለመታደግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሊያሰማራ ያቀደውን ከሃገራት የተውጣጣ ኃይል ለመምራት ኬንያ ያሳየችውን ፈቃደኝነት በተመለከተ ትኩረት እንደሚያደርጉ ታውቋል።

ኬንያ አንድ ሺሕ የሚሆን የፖሊስ ኃይሏን እንደምታሰማራ ቃል የገባች ሲሆን፣ አሜሪካ እና ሌሎች ሃገራት ግን የጦር ኃይላቸውን በሄይቲ ማሰማራት እንደማይሹ አስታውቀዋል።

የመጀመሪያው ዙር የኬንያ ፖሊስ ኃይልም፣ በወሮበሎች በመናጥ ላይ ባለችው የሄይቲ መዲና ፖርት ኦ ፕሪንስ በዚህ ሳምንት እንደሚደርስ ይጠበቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG