በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለሩት ባደር ጊንስበርግ የመታሰቢያ ሃውልት ሊቆም ነው


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሩት ቤደር ጊንስበርግ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሩት ቤደር ጊንስበርግ

ለሟቿ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሩት ቤደር ጊንስበርግ በተወለዱበት እና ባደጉበት በኒው ዮርክ ከተማ ብሩክሊን ቀበሌ መታሰቢያ ሃውልት እንደሚቆምላቸው የክፍለ ግዛቷ ሃገረ ገዢ አንድሩው ኮሞ አስታውቀዋል።

ሃውልቱን የሚቀርጸውን የኪነ ጥበብ ባለሙያ እና የት ቦታ እንደሚቆም የሚመርጥ ኮሚሽን እንደሚሰይሙ ኮሞ አስታውቀዋል።

ለሩት ጊንስበርግ የሚሰራላቸው ሃውልት ላበረከቱት ታላቅ አሰተዋጽዖ ቋሚ መታሰቢያቸው ይሆናል፤ የርሳቸውን ታላላቅ ሥራዎች ለማስቀጠል ለሚሰሩ ሌሎችም ማበረታቻ ይሆናል ብለዋል።

XS
SM
MD
LG