በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያዊው ጋዜጠኛ የኖቤል ሽልማቱን ለዩክሬን ህጻናት መርጃ ይውል ዘንድ በሚል ለጨረታ አቀረበ


ሩሲያዊው ጋዜጠኛ ዲሚትሪ ሙራቶቭ
ሩሲያዊው ጋዜጠኛ ዲሚትሪ ሙራቶቭ

የዚያ ጥያቄ መቋጫ ዛሬ ሩሲያዊው ጋዜጠኛ ዲሚትሪ ሙራቶቭ የኖቤል የሰላም ሽልማቱን ሜዳሊያ በጨረታ በመሸጥ ገቢው በዩክሬን በጦርነት ሳቢያ የተፈናቀሉ ህጻናትን ለመርዳት ዓለም አቀፉ ሕጻናት አድን ድርጅት ድርጅት ዩኒሴፍ ለሚያደርገው መደጎሚያ ሲውል ይመለሳል።

ሙራቶቭ በሃገሩ ሩሲያ የንግግር ነጻነትን ለማራመድ በተባባሪነት ባቋቋመው እና በዋና አዘጋጅነት ይመራው በነበረው የሩሲያ ነፃ ጋዜጣ ኖቫያ አማካኝነት ላበረከተው አስርተዋጾ በሚል እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ባለፈው ጥቅምት 2021 ነው የኖቤል ሽልማቱ አካል የሆነውን የወርቅ ሜዳሊያ የተሸለመው።

ጋዜጣው ሩሲያ ዩክሬን በወረረች ማግስት መንግሥት በጋዜጠኞች እና በተቃዋሚዎች ላይ እርምጃ ከወሰደበት ካለፈው መጋቢት ወር አንስቶ እንደተዘጋ ነው። ሙራቶቭ ከዚህ ጋር የተያያዘውን የ500 ሺህ ዶላር የገንዘብ ሽልማትም ለበጎ አድራጎት እንደሚለግስ አስቀድሞ ይፋ አድርጓል። ሽልማቱን ለጨረታ የማውጣትም ሆነ የልገሳው ሃሳብ “ለህፃናት ስደተኞች የወደፊት ዕጣ እድል ለመስጠት ነው” ሲል አስረድቷል።

ሙራቶቭ ከአሶሼትድ ፕሬስ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ በተለይ በዩክሬን በተፈጠረው ግጭት ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት ጉዳይ ያሳስበኛል ማለቱም ተዘግቧል።

ዛሬ ማለዳ ድረስ ጨረታ ለቀረበው የኖቤል ሽልማት የወርቅ ሜዳሊያ የተሰጠው ከፍተኛው የመግዣ ዋጋ 550 ሺህ ዶላር ነበር። በሚሊዮኖች ሊሸጥ እንደሚችል ተገምቷል።

XS
SM
MD
LG