በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተስፋ ያደረጉት ተቃዋሚ ያሰባሰቡትን ፊርማ አቀረቡ


ተቃዋሚው ቦሪስ ናዴዥዲን
ተቃዋሚው ቦሪስ ናዴዥዲን

ለሩሲያው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሺዎች በሚቆጠሩ ሩሲያውያን የተደገፉት ተቃዋሚው ቦሪስ ናዴዥዲን ወደ ቀጣዩ የምርጫ ሂደት ለማለፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሰበሰቡ ፊርማዎችን ዛሬ ረቡዕ ለማዕከላዊ ምርጫ ኮሚሽን አቅርበዋል።

የምርጫ ኮሚሽኑ ናዴዥዲን ለምርጫው ተወዳዳሪነት መመዝገብ ይችሉ አይችሉ እንደሆነ ለመወሰን ሰነዶችን ይገመገማል ተብሎ ይጠበቃል።

በሞስኮ አቅራቢያ በምትገኝ ከተማ ውስጥ የአካባቢ ህግ አውጭ ሆኖ የሚያገለግሉት እና ለዘብተኛ ፖለቲካ የሚያራምዱት የ60 ዓመቱ ናዴዥዲን፣ በዩክሬን ያለው ጦርነት እንዲቆም እና ከምዕራቡ ዓለም ጋር ውይይት እንዲጀመር በይፋ ጠይቀዋል።

በመላው ሀገሪቱ ከጎናቸው የተሰለፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሩሲያውያንም የናዴዥዲን እጩነት በመደገፍ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ በብርቱ ቁጥጥር ስር ባለ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ያልተለመደው ተቃውሞ መታየቱ ለክሬሚሊን ፈተና አስነስቷል፡፡ ደጋፊዎቻቸውን ያመሰነጉት ናዴዥዲን የማዕከላዊ ምርጫ ኮሚሽን እጩ አድርጎ እንደሚመዘግባቸው ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

ፊርማዎችን ካቀረቡ በኋላ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ "በዚህ ጉዳይ ላይ የማዕከላዊ ምርጫ ኮሚሽን የሚመራው በመንገደኛ ሳይሆን በመርህ ሂደቱ ነው ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። እጩው ናዴዥዲን በመቶ ሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች እንደሚደገፍ ማንም አይጠራጠርም ብለዋል፡፡

"ምንም ቢፈጠር" ያልተፈቀዱ ሰልፎችን ፈጽሞ እንደማይጠሩ የተናገሩት ናዴዥዲን “ይሁን እንጂ ግን በህገ-መንግስቱ መሠረት ሁሉም የሩሲያ ዜጎች፣ በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብ እና በህግ በተደነገገው መንገድ ሃሳባቸውን የመግለጽ መብት አላቸው፡፡” ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG