በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር በዓመታዊ ንግግራቸው የጦራቸውን ስኬት አወደሱ


የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሐሙስ እለት ባደረጉት ዓመታዊ ንግግር፣ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ሲሉ የጠሩት ጦርነት በተካሄደበት ወቅት የአገራቸው ጦር ያሳየውን ስኬት አወድሰዋል።

የሩሲያ የኒዩክሌር ኃይሎች "በሙሉ ዝግጁነት" ላይ ናቸው ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው የተናገሩት ፑቲን ጦሩ አዳዲስ ጠንካራ መሳሪያዎችን ማዘጋጀቱን እና አንዳንዶቹም በዩክሬን ጦርነት ውስጥ መፈተሻቸውን ገልጸዋል።

ፑቲን በሐሙሱ ንግግራቸው የሞስኮን ግቦች በዩክሬን ለመፈጸም ቃል የገቡ ሲሆን ምዕራባውያን በጦርነቱ ውስጥ ጥልቅ ተሳትፎ እንዳይኖራቸው በጥብቅ አስጠንቅቀዋል።

ፑቲን ማስጠንቀቂያውን ያስተላለፉት በሚቀጥለው ወር ከሚካሄደው እና እንድሚያሸንፉ እርግጠኛ ከሆኑበት ምርጫ ቀደም ብለው ሲሆን ሪሲያ በዩክሬን የሚኖራትን የበላይነት ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆናቸውንም አስምረውበታል።

የሩሲያን ወታደሮች በማወደስም በጦርነት ለተሰዉት ተዋጊዎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት አድርገዋል።

ፑቲን እአአ በ2022 ወታደሮቻቸውን ወደ ዩክሬን የላኩት የሩሲያን ጥቅም ለማስከበር እና ዩክሬን ኔቶን በመቀላቀል ለሩሲያ የደህንነት ስጋት እንዳትፈጥር ለመከላከል እንደሆነ ደጋግመው ይገልፃሉ። ኪየቭ እና አጋሮቹ ግን ያለምክንያት የተፈፀመ ወረራ ነው በማለት ያወግዙታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG