በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያና የሶሪያ መሪዎች በሶሪያ ጦርነት ፖለቲካ መፍትሄ ላይ ተወያዩ

የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን እና የሶሪያው መሪ ባሻር አል አሳድ
የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን እና የሶሪያው መሪ ባሻር አል አሳድ

ትናንት ሰኞ ሶቺ ከተማ ላይ አስቀድሞ ያልተገለፀ ስብሰባ ያደረጉት የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን እና የሶሪያው መሪ ባሻር አል አሳድ ለሶሪያ ጦርነት ፖለቲካዊ መፍትሄ ማግኘት ላይ ማትኮር እንደሚያስፈልግ ተነጋግረዋል።

ትናንት ሰኞ ሶቺ ከተማ ላይ አስቀድሞ ያልተገለፀ ስብሰባ ያደረጉት የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን እና የሶሪያው መሪ ባሻር አል አሳድ ለሶሪያ ጦርነት ፖለቲካዊ መፍትሄ ማግኘት ላይ ማትኮር እንደሚያስፈልግ ተነጋግረዋል።

መሪዎቹ ተገናኝተው መወያይታቸውን ሁለቱ ሀገሮች ይፋ ያደረጉት ዛሬ ነው። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ሚስተር ፑቲንና ሚስተር አሳድ ያደረጉት ውይይት ሩስያ ከቱርክና ከኢራን ባለሥልጣናት ጋር ተግባራዊ የሚሆን ሥምምነት ላይ መድረስ መቻሏን ለማረጋገጥ እንደሚጠቅም አመልክተዋል።

ሚስተር ፑቲን ሶሪያ ውስጥ የሚካሄደው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ሊጠናቀቅ ተቃርቡዋል ማለታቸውን የተናገሩት ክሪምሊንና የሶሪያ መንግሥት የዜና አገልግሎት የሩስያው ፕሬዚዳንት አሳድን በሽብርተኞች ላይ የተሳካ ጦርነት ስላካሄዱ እንኳን ደስ ያለዎ እንዳሉዋቸው አክለው ገልፀዋል።

ትናንት ሶቺ ላይ ለአራት ሰዓታት ያህል የቆዩት አሳድ መሪዎች በፖለቲካዊ መፍትሄው ረገድ ርምጃ እንደሚኖር አሁን ጦርነቱ ያለበት ይዞታ ያመላክታቸዋል የሚል ዕምነት እንዳላቸው የሩስያ ዜና ማሰራጫዎች ዘግቧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG