በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩስያ ፕሬዚደንት: "ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር እፈልጋለሁ"


የሩስያ ፕሬዚደንት ቪላዲሚር ፑቲን በመጪው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አሸናፊው ማንም ቢሆን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር እፈልጋለሁ ሲሉ ተናገሩ።

የሩስያ ፕሬዚደንት ቪላዲሚር ፑቲን በመጪው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አሸናፊው ማንም ቢሆን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር እፈልጋለሁ ሲሉ ተናገሩ። ፑቲን ከኣለም ኣቀፍ ጋዜጠኞች ጋር በሚያካሂዱት ዕመታዊ ጋዜጣዊ ጉባዔ ከማንኛውም የኣሜሪካ ህዝብ ከሚመርጠው ፕሬዚደንት ጋር አብሬ ለመስራት ዝግጁ ነኝ ብለዋል።

አያይዘውም ሚስተር ፑቲን በዚህ ሳምንት ውስት ከዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጃን ኬሪ ያካሄድኩት ውይይት "ዩናይትድ ስቴትስ በጋራ ጥረት ብቻ ሊፈቱ የሚችሉ ጉዳዮችን ወደመፍታት ኣቅጣጫ ኣያመራች መሆኑዋን ተረድቼበታለሁ" ብለዋል።

ሶሪያን በተመለከተ ደግሞ ፑቲን ፖሌቲካዊ ሂደት ኣስኪጀመር ሀገራቸው ወታደራዊ ዘመቻዋን እንደምትቀጥል ገልጸው።

XS
SM
MD
LG