ዋሺንግተን ዲሲ —
በፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ላይ አድማ አቀነባብረዋል ተብለው ባለፈው ወር የታሰሩት ሩስያዊው ተቃዋሚ መሪ አሌክሲ ናቫልኒ፣ ከ30 ቀናት እስር በኋላ በዛሬው ዕለት መፈታታቸው ተገለፀ።
«ከ30 ቀናት የሥራ ጉዞ በኋላ እነሆ ተመልሻለሁ» ሲሉ ትዊት ያደረጉት ናቫልኒ፣ “ነፃ በመሆኔ ተደስቻለሁም” ብለዋል።
ናቫልኒና በመቶዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው የታሰሩት ባለፈው ወር ሲሆን፣ ይህም ፕሬዚዳንት ፑቲንን ለሌላ ሥድስት ዓመት በሥልጣን ለማቆየት የሚያስችለው ሥነ ሥርዓት ሞስኮ ውስጥ በሚካሄድበት ዋዜማ መሆኑ ነው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ