በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያው ላቭሮቭ ሲናገሩ ምዕራባዊያኑ ጥለው ወጡ


የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ(በስክሪኑ ላይ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በቪድዮ ኮንፈረንስ ንግግር ሲያደርጉ ጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ እአአ መጋቢት 1/2022
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ(በስክሪኑ ላይ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በቪድዮ ኮንፈረንስ ንግግር ሲያደርጉ ጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ እአአ መጋቢት 1/2022

ዛሬ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ መናገር ሲጀምሩ በምክር ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ከነበሩ ተሳታፊዎች ብዙዎቹ ተነስተው ወጥተዋል።

ላቭሮቭ ለዚህ የተሳታፊዎች አድራጎት የተዘጋጁ አለመምሰሉና ንግግራቸውን ምክር ቤቱ ፊት በአካል ከመገኘት ይልቅ በቪድዮ ኮንፈረንስ እንዲያደርጉ መገደዳቸውን መናገራቸውን ሊሳ ሽላይን ከጄኔቫ ለቪኦኤ በላከችው ዘገባ አስፍራለች።

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በንዴት መንፈስ መናገራቸውንና ወደ ጄኔቫ ለመጓዝ በሰማዮቻቸው ላይ እንዳይበርሩ ሃገሮቹ መከልከላቸውን፣ በዚህም የአውሮፓ ኅብረት የመንቀሳቀስ ነፃነታቸውን መጋፋቱን መግለፃቸውን ሊሳ ዘግባለች።

ላቭሮቭ ለስምንት ደቂቃ በቆየ ንግግራቸው “በዋሺንግተን ይመራል” ያሉትን “የምዕራቡን የጋራ ፖሊሲ” ሲያወግዙ ይህም “የኪየቭን አገዛዝ ላለፉት 14 ዓመታት በራሱ ህዝብ ላይ ጦርነት እንዲያካሂድ አድርጎታል” ብለዋል።

የዩክሬኑን አስተዳደር በወንጀል አድራጎቶች የኮነኑት ሚስተር ላቭሮቭ “በሩሲያና ተገንጣዮቹ ዳኔትስክና ሉሃንስክ ውስጥ ባሉ ሩሲያኛ ተናጋሪ ዜጎቹ ላይ ባለፉት ስምንት ዓመታት ጦርነት አውጆ ቆይቷል” ሲሉ ከስሰዋል። ይህ ክሳቸው ከበዛው የዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ አመለካከት ጋር እንደሚጣረስ ተዘግቧል።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን “ዕጣ ፈንታቸውን በግድ የለሽነት እያዩ መቀጠል ባለመቻላቸው ለአካባቢዎቹ ነፃነት ዕውቅና ሰጥተው “ነዋሪዎቻቸውን ከአደጋ ለመጠበቅ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ከፍተዋል” ብለዋል።

ይህንን ቀደም ሲልም በፕሬዚዳንት ፑቲን በራሳቸው የተነገረ ሰበብ “ማሳሳቻ ሃሰተኛ መረጃ የማሠራጨት ዘመቻ” ሲሉ ያጣጣሉት ምዕራባዊያን መንግሥታት ለወረራው ታይቶ በማይታወቅ ስፋት ምላሽ ሰጥተዋል።

ሚስተር ላቭሮቭ በእነሱም ላይ ውግዘት አሰምተዋል።

ላቭሮቭ እየተናገሩ ሳሉ መግለጫ የሰጡት የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቃል አቀባይ ሻቢያ ማንቱ ጦርነቱን የሚሸሹት ዩክሬናዊያን ስደተኞች ቁጥር እጅግ በተፋጠነ ሁኔታ ማሻቀቡን ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG