በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩስያ ምርጫ


የሩስያው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሥርዓት ባለው መንገድ ተከናውኗል፣ ነገር ግን ለድምፅ ሰጪው የቀረበለት አማራጭ አልነበረም ሲል የአውሮፓ ፀጥታ እና ትብብር ድርጅት ተናገረ።

የሩስያው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሥርዓት ባለው መንገድ ተከናውኗል፣ ነገር ግን ለድምፅ ሰጪው የቀረበለት አማራጭ አልነበረም ሲል የአውሮፓ ፀጥታ እና ትብብር ድርጅት ተናገረ።

የድርጅቱ የምርጫ ታዛቢዎች ባወጡት መግለጫ በተካሄደው የተጧጧፈ ቅስቀሳ የሀገሪቱ ዜጎች በብዛት ወጥተው ድምፅ መስጠታቸውን ገልፀዋል። ይሁን እንጂ በመሰረታዊ መብቶች እና በዕጩዎች ምዝገባ ላይ የተጣሉት ገደቦች የፖለቲካ ተሳትፎውን መድረክ በማጥበቡ እውነተኛ የምርጫ ፉክክር ሊኖር እንዳልቻለ አመልክተዋል።

የሩስያ ፕሬዚዳንት ቪላዲሚር ፑቲን ሰባት ሌሎች ተወዳዳሪዎችን አሸንፈው በከፍተኛ ቁጥር ሊመረጡ እየተንደረደሩ ናቸው።

ትናንት ዕሁድ ማታ ክሬምሊን ቤተ መንግሥት አጠገብ በሚገኘው ማኔዥናያ አደባባይ በሽሕዎች ለተቆጠረ ህዝብ ንግግር ያደረጉት ፑቲን ለርሳቸው ድምፅ የሰጡትን ሰዎች

“ትልቁ ሀገርቀፍ ስብስባችን” ሲሉ አሞግሰው ዓላማችንን በስኬት እናከናውነዋለን ሲሉ ቃል ገብተዋል።

“በቀጣይነት መወዳደር በሚችሉበት እኤአ በ2030 ይወዳደራሉ ወይ?” ተብለው ሲጠየቁ የሥድሳ ዓመቱ ፑቲን

“አስቂኝ ጥያቄ ነው መቶ ዓመት እስኪሆነኝ እዚህ ቁጭ የምል ይመስልሃል” ማለታቸው ተጠቅሷል።

የሚስተር ፑቲን ዋና ተፎካካሪያቸው ባለፈው ታኅሣሥ ወር በገንዘብ ምዝበራ ክስ ተፈርዶባቸው፣ እንዳይወዳደሩ የታገዱት ተቃዋሚ መሪ አሌክሲ ናቫልኒ ነበሩ። ናቫልኒ የተፈረደብኝ ከምርጫው ለማስወጣ ሆን ተብሎ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG