በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የሩሲያ ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር ታሰሩ


የቀድሞው የመከላከያ ምክትል ሚኒስትር ፓቬልፖፖቭ
የቀድሞው የመከላከያ ምክትል ሚኒስትር ፓቬልፖፖቭ

የቀድሞው የመከላከያ ምክትል ሚኒስትር ፓቬልፖፖቭ በማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው ትላንት ሐሙስ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሩሲያ መንግስት ዜና ማሰራጫ ዘግቧል።

ፖፖቭ በተጠረጠሩበት ወንጀል ክስ ከተመሰረተባቸው እና ከተፈረደባቸው እስከ 10 አመት እስራት ይጠብቃቸዋል።

በፖፖቭ ላይ የተመሰረተው ክስ፣ሞስኮ በሚገኘው የፓትሪዮትፓርክ ውስጥ ከሚገኙ የንግድ እንቅስቃሴዎች ጋር የተያያዘ ነው፡፡

በወጣት ሩሲያውያን መካከል የሀገር ፍቅር ስሜትን ለመፍጠር የተቋቋመው የአርበኞች ፓርክ የአውሮፕላን ማረፊያ ፣ ሙዚየሞች እና ለሩሲያ ጦር ኃይሎች የተሠራካቴድራል አለው።

ፖፖቭ እኤአ ከ2013 እስከ ሰኔ 2024 ድረስ በፕሬዝዳንቱ ውሳኔ እስከተሰናበቱበት ጊዜ ድረስ የሩሲያ የመከላከያ ምክትል ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።

የሳቸው እስር በሩሲያ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ላይ ከተፈጸመው እስር የቅርብ ጊዜ ነው፡፡

የፖፖቭ እስራት በሩሲያ የጦር ኃይሎች የላይኛው አመራር ውስጥ ሥልጣንን አላግባብ በመጠቀም ላይ የሚካሄድ ሰፊ ዘመቻ ይመስላል፡፡

ከቅርብ ወራት ወዲህ በጉቦ፣ በማጭበርበር እና ስልጣንን ላይ ያለአግባብ ከመጠቀም ጋር በተገናኘ ክስ ተጠርጥረው ሲታሰሩ፣ የቀድሞው ባለስልጣን ስምንተኛው ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር ናቸው፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG