በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ የመከላከያ ሚንስትር "የምስራቅ ዩክሬን ባኽሙት ከተማን መያዝ ያስፈልገናል" አሉ


የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ

የሩሲያ ኃይሎች ዩክሬን ዶንባስ ክፍለ ግዛት ውስጥ ገፍተው ለሚያካሂዱት ጥቃት ባኽሙት ከተማን መቆጣጠር ይኖርባቸዋል ሲሉ የመከላከያ ሚንስትሩ ተናገሩ። የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ በበኩላቸው ባኽሙት ላይ መዋጋታችንን እንቀጥላለን ሲሉ ዝተዋል።

የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስትር ሴርጌ ሾይጉ ዛሬ ለጦር ሰራዊቱ ባለሥልጣናት ባደረጉት ንግግር ባኽሙት ለዩክሬን ኃይሎች መክተው የሚውጉባት ቁልፍ ቦታ መሆኗን ገልጸው የሩስያ ኃይሎች ወደውስጥ ዘልቀው ለማጥቃት ከተማዋን መያዝ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ በበኩላቸው የጦር አዛዦቻቸው በሙሉ በአንድ ድምጽ ባኽሙት ላይ ውጊያውን መቀጠል አለብን ማለታቸውን ገልጸዋል። የምስራቅ ዩክሬኗ ከተማ ለወራት ከባድ ውጊያ ሲካሄድባት ቆይቷል።

ትናንት የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስተን በሰጡት ቃል የሩሲያ ኃይሎች ከተማዋን ቢቆጣጠሯት በጦርነቱ ይዞታ ላይ የሚያመጣው ወሳኝ ለውጥ እንደማይኖር ተናግረው ነበር።

የጦርነት ጥናት ተቋም የተባለ ዋሽንግተን የሚገኝ የምርምር ተቋም የዩክሬን ወታደሮች ከባኽሙት ታክቲካዊ የማፈግፈግ ዕርምጃ የወሰዱ እንደሚመስል ተናግሯል፡፡ ሆኖም ሙሉ በሙሉ ለቅቀው ለመውጣት እየተንቀሳቀሱ ነው የሚል ድምዳሜ ከወዲሁ ለመስጠት እንደማይቻል አክሏል፡፡

XS
SM
MD
LG