በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ ፍ/ቤት ለአሜሪካዊ የዋስ መብት እንዳይሰጥ ከለከለ


ፎቶ ፋይል፡- የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ባህር ኃይል ባልደረባ ፖል ዊላን
ፎቶ ፋይል፡- የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ባህር ኃይል ባልደረባ ፖል ዊላን

አንድ የሩሲያ ፍ/ቤት በሥለላ ወንጀል ለተከሰሰው አሜሪካዊ የዋስ መብት እንዳይሰጠው ከለከለ።

አንድ የሩሲያ ፍ/ቤት በሥለላ ወንጀል ለተከሰሰው አሜሪካዊ የዋስ መብት እንዳይሰጠው ከለከለ።

የሩሲያ ፌዴራል ፖሊስ ስለ ጉዳዩ ሲገልፁ ጥንድ የአሜሪካና እንግሊዝ ዜግነት ያለውና የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ባህር ኃይል ባልደረባ ፖል ዊላን ባለፈው ወር ተይዞ የታሠረው በሥለላ ተግባር ተሠማርቶ በመገኘቱ ነው ብሏል። ዊላን በትክክል ምን ዓይነት የሥለላ ተግባር ሲፈፅም እንደተገኘ ግን ፖሊስ ዝርዝር አልሰጠም።

የዊላን ቤተሰቦች - ከቀረበበት የወንጀል ክስ ነፃ መሆኑን ያስረዳሉ።

የ48 ዓመት ዕድሜ ያለው ፖል ዊላን ዛሬ በአንድ የሞስኩ ፍ/ቤት የቀረበው በዋስ እንዲፈታና ጉዳዩ እንዲቀጥል ለማድረግ ነበር። ዳኛው ጥያቄውን ውድቅ አድርገው ወደ እሥር ቤት መልሰውታል።

ሩስያ ምናልባት ከክሬምሊን ቤተ መንግሥት በሚሰጣት ትዕዛዝ በአሜሪካ የወግ አጥባቂ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ሠርጋ በመግባት ሥለላ እንድታካሂድ መመደቧን ያመነችውን ማሪያ ቡቲናን ለማስለቀቅ ስትል ነው ፖል ዊላንን ያሠረችው የሚል ጭምጭምታ አለ።

ክሬምሊን ግን - ዊላንን በሩሲያ እሥረኛ የመለውጥ ሃሳብ አለ የሚለውን ግምት ውድቅ አድርጓል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG