በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጣሊያን ታስሮ የነበረው ሩሲያዊ ባለሀብት አምልጦ አገሩ ገባ


ፎቶ ፋይል፦ ሮም፣ ጣሊያን የሚገኝ ፍርድ ቤት
ፎቶ ፋይል፦ ሮም፣ ጣሊያን የሚገኝ ፍርድ ቤት

በአሜሪካ በሕግ ይፈለግ የነበረና በጣሊያን በቤት ውስጥ እስር ላይ የነበረ አንድ ሩሲያዊ ባለሀብት፣ አምልጦ ወደ አገሩ ከገባ በኋላ ዛሬ ማክሰኞ ተከሥቷል።

አሜሪካ፣ በሩሲያ ባለሥልጣናት እና ባለሀብቶች ላይ በጣለችው ማዕቀብ ከሚፈለጉት አንዱ የነበረው የ40 ዓመቱ አርቲዮም ኡስ፣ ባለፈው ጥቅምት ጣሊያን ውስጥ ተይዞ በቤት ውስጥ እስር ላይ እንዲቆይ ተደርጎ ነበር።

“የጣሊያን ፍ/ቤቶች፣ በአሜሪካኖቹ ጫና አሳልፈው ሊሰጡኝ ስለሚችሉ አምልጫለኹ፤” ሲል ተናግሯል ኡስ።

ክራስኖያርስክ የተባለው ክልል አገረ ገዢ ልጅ የኾነው አርቲዮም ኡስ፣ የተጣለውን ማዕቀብ በመጣስ፣ የምዕራባውያንን ቴክኖሎጂ ወደ ሩሲያ ሲያስገባ ነበር፤” ተብሏል። አሜሪካም፣ በዚኹ ጥሰት ምክንያት ተላልፎ እንዲሰጣት ጠይቃ ነበር።

ኡስ፣ ባለፈው ታኅሣሥ፣ ከእስር ቤት ሚላን ዳርቻ ወደሚገኝ የቤት ውስጥ እስር ተዛውሮ ነበር።

የጣሊያን ፍርድ ቤት፣ “ግልጽ የኾነ ፖለቲካዊ አድልዎ አሳይቷል፤ ለአሜሪካም ግፊት የመታዘዝ ዕድል ነበረው፤” ሲል ኡስ መናገሩን አሶስዬትድ ፕረስ ዘግቧል።

ካለፈው ወር ወዲህ፣ ኡስ የት እንደገባ አይታወቅም ነበር። በዛሬው ዕለት፣ በሩሲያ ውስጥ እንደሚገኝ፣ ለአንድ መንግሥታዊ የዜና አገልግሎት እስከሚገልጽ ድረስ፡፡

“አሁን ባለው ዓለም አቀፍ ኹኔታ፣ ኹሉም ከእኛ በተፃራሪ በቆመበት ወቅት፣ የእኔ ማምለጥ ድል ነው፤” ብሏል በአድራጎቱ የተኩራራው ኡስ።

የጣሊያን ብዙኀን መገናኛዎች፣ በኡስ ማምለጥ ጉዳይ፣ የሩሲያ የስለላ ወኪሎች እንዳሉበትና እግሩ ላይ የተገጠመውን መከታተያ መሣሪያ በመፍታት፣ በሐሰተኛ ፓስፖርት እና በተሽከርካሪ እገዛ ከአገር እንዳስወጡት ጠቅሰዋል፤ ከዚያም፣ በግል አውሮፕላን ወደ ሩሲያ እንደወሰዱት ዘግበው ነበር።

የሩሲያ ባለሥልጣናት፣ በጣሊያን ብዙኀን መገናኛ ዘገባ ላይ ያሉት ነገር የለም።

XS
SM
MD
LG