በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሞስኮ ምርጫ


ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን
ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን

ሞስኮ በተካሄደው ምርጫ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን፣ እአአ እስከ 2036 ድረስ፣ በሥልጣን ሊቆዩ የሚችሉበትን ዕድል የሚያካትት፣ የሕገ መንግሥታዊ ለውጥ ፀደቀ። መራጮች 77.9 በ21.3ከመቶ እንዳጸደቁት ተገልጿል።

የክረምሊን ቤተ-መንግሥት ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ዛሬ ሲናገሩ፣ በምርጭው ውጤት ድል ተገኝቷል ብልዋል።

የተቃውሞ ባለሥልጣኖችና ታዛቢዎች በምርጫው ሂዳት ህጋዊነት ላይ፣ የጥርጣሬ ስሜት አንጸባርቀዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች በምርጫው የተሳተፉት ስዎች ብዛት፣ አጠራጥሪ ነው። ሌሎች ስጋቶችም አሉ ብለዋል።

አሌክሲ ናቫለኒ የተባሉ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ፣ ምን ጊዜም ቢሆን ለምርጫው ውጤት እውቅና አንሰጥም ብለዋል። የሀገሪቱ የምርጫ ባለሥልጣኖች ግን፣ ምርጫው በተአማኒነት ተካሂዷል ብለዋል።

የ67 ዓመት ዕድሜው ፑቲን፣ ሩስያን በጠቅላይ ሚኒስትርነትና በፕሬዚዳንትነት፣ ለሁለት አሥርተ ዓመታት ያህል መርተዋል። አሁን በፀደቀው ሕገ መንግሥት መሰረት ደግሞ፣ የአሁኑ ሥልጣናቸው ከ4 ዓመታት በኋላ ሲያበቃ፣ ለሁለት ተከታታ 6 ዓመታት ሊወዳደሩ ይችላሉ።

XS
SM
MD
LG