በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ሩሲያ ከፓሪሱ ኦሎምፒክ አትቀርም" - የሩሲያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ


የሩሲያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ስታኒስላቭ ፖዝድኖያኮቭ
የሩሲያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ስታኒስላቭ ፖዝድኖያኮቭ

"ዘንድሮ በፓሪስ ከሚደረገው የኦሎምፒክ ውድድሮች ሩሲያ አትቀርም" ሲል የሩሲያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዛሬ ሐሙስ አስታወቀ። የኦሎምፒክ ኮሚቴው ፕሬዚዳንት ስታኒስላቭ ፖዝድኖያኮቭ በሩሲያው የዩክሬን ወረራ ምክንያት በአንዳንድ የሩሲያ አትሌቶች ላይ ዓለም አቀፉ የኦሎሚፒክ ኮምቴ ያሳለፈው የገደብ ቅጣት ቢኖርም ሩሲያ ከኦሎምፒኩ ራሷን እንደማታገል አስታውቀዋል፡፡

“ራስን ከውድድሮቹ የማገለልን መንገድ በፍጹም አንከተልም” ያሉት ፕሬዚዳንቱ “ሁልጊዜም አትሌቶቻችንን እንደግፋለን” ሲሉ ለሩሲያ መንግሥት የዜና አገልግሎት በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል፡፡

“ይሁን እንጂ በዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች ሕጋዊና ፍትሃዊ ያልሆኑ ፍጹም ተቀባይነት የሌላቸው መሆናቸውን አበክረን እንገልጻለን።”ሲሉ ፕሬዚዳንቱ አክለው ተናግረዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የፈቀደው፣ እኤአ ከሀምሌ 26 እስከ ነሀሴ 11 በሚካሄዱ የፓሪስ የኦሎምፒክ ስፖርታዊ ውድድሮች ሩሲያውያን እና ቤላሩስያውያን የአገራቸው ሰንደቅ ዓላማ፣ አርማ ወይም ብሄራዊ መዝሙር ሳይዙ በገለልተኝነት እንዲሳተፉ መሆኑን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

“ይሁን እንጂ በዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች ሕጋዊና ፍትሃዊ ያልሆኑ ፍጹም ተቀባይነት የሌላቸው መሆናቸውን አበክረን እንገልጻለን።”

ገለልተኛ የተባሉት አትሌቶች በግል ስፖርቶች ብቻ የሚወዳደሩ ሲሆን ለሁለቱም ሀገራት ምንም አይነት የቡድን ውድድሮች አልተፈቀደም፡፡

በዩክሬን ውስጥ ያለውን ጦርነት የሚደግፉ ከሩሲያ ወይም ከቤላሩስ ጦር ጋር ኮንትራት ያላቸው አትሌቶች በውድድሩ እንዲሳተፉ አይፈቀድላቸውም። ሩሲያ እገዳዎቹን አጥብቃ ተቃውማለች።

የፓሪስ ከንቲባ አኔ ሂዳልጎ ለሮይተርስ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ ሩሲያውያን እና ቤላሩስያውያን “ባይመጡ” እንደሚመርጡ ተናግረዋል፡፡

“የሩሲያን የዩክሬን ወረራ እንዳልተፈጸመ አድርገን መንቀሳቀስ አንችልም” ሲሉም ከንቲባዋ አክለዋል። ሩሲያና ቤላሩስ እኤአ የካቲት 2022 ከተፈጸመው የሩሲያ ወረራ ማግስት ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚደረጉ ውድድሮች ታግደዋል፡፡

ባላፈው ታህሳስ፣ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የፓሪሱን የኦሎሞፒክ ጨዋታዎች አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ አትሌቶቹ በተናጥል የሚያደርጉትን ውድድር የሚደግፉ ቢሆንም፣ ዝግጅቱ የሩሲያን ስፖርት “እየሞተ” አድርጎ ለማሳየት የሚሞክር ከሆነ፣ “ሩሲያ በውድድሩ የመሳተፉን ጉዳይ ታስብበታለች” ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG