በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ለሚደረግ የእስረኛ ልውውጥ ሥምምነት እየተሟሟቀች ነው


የዩናይትድ ስቴትሷ የቅርጫት ኳስ ኮከብ ብሪትኒ ግሪነርን
የዩናይትድ ስቴትሷ የቅርጫት ኳስ ኮከብ ብሪትኒ ግሪነርን

ሩሲያ ዛሬ አርብ ይፋ እንዳደረገችው ሞስኮ ላይ እስር ላይ የምትገኘውን የዩናይትድ ስቴትሷን የቅርጫት ኳስ ኮከብ ብሪትኒ ግሪነርን ሊያካትት በሚችል የእስረኛ ልውውጥ ሥምምነት በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘውን እና “የሞት ነጋዴ” በሚል ቅጽል መጠሪያ የሚታወቀውን ሩሲያዊ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ቪክቶር ቦውትን ለማስፈታት ተስፋ አድርለች።

አውሮፓ ውስጥ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ እጅግ የከፋው የተባለው ጦርነት እየተካሄደ ባለበት ባሁኑ ወቅት ሩሲያ እና ዩናይትድ ስቴትስ ግሬነርን ጨምሮ በሩስያ እስር ቤት የሚገኙ አሜሪካውያንን በቦውት ምትክ አስፈትቶ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የሚያደርግ የእስረኞች ልውውጥ ሃሳብ እያወጡ እያወረዱ መሆናቸው ነው የተዘገበው።

የሩሲያው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ሪያብኮቭ፣

“ተስፋው ተስፋ ብቻ ሆኖ የሚቀር ሳይሆን እየተጠናከረ የመጣ እና ከአንዳች ሁነኛ ሥምምነት ላይ እንደምንደርስ ተስፋ ማድረግ እፈልጋለሁ” ሲሉ ለሩሲያው ኢንተርፋስ የዜና ወኪል መናገራቸው ተዘግቧል።

XS
SM
MD
LG