በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ አሜሪካዊ ጋዜጠኛዋ የእስር ጊዜ ተራዘመ


ሩሲያ አሜሪካዊ ጋዜጠኛ አልሱ ኩርማሼቫ
ሩሲያ አሜሪካዊ ጋዜጠኛ አልሱ ኩርማሼቫ

ሩሲያ አሜሪካዊ ጋዜጠኛ አልሱ ኩርማሼቫ ለተጨማሪ ሁለት ወራት በእስር እንድትቆይ አንድ የሩሲያ ፍ/ቤት ዛሬ ወስኗል።

ጋዜጠኛዋ የውጪ ወኪል መሆኗን ሳታስመዘግብ የሩሲያ መከላከያን በተመለከተ መረጃን ስብስባለች በሚል ባለፈው ሰኔ በሩሲያ የፀጥታ ኃይሎች በአውሮፕላን ማረፊያ ሳለች ፓስፖርቷ ተነጥቆ ለአጭር ጊዜ ታግታ ነበር፡፡ በኋላም በጥቅምት ወር ለእስር ተዳርጋለች፡፡

አልሱ ኩርማሼቫ በአሜሪካ መንግስት በጀት በሚንቀሳቀሱትና የአሜሪካ ድምፅ እህት የሚዲያ ተቋማት የሆኑት የነፃ አውሮፓ ራዲዮ እና የነፃነት ራዲዮ ባልደረባ ነች፡፡

ጥምር ዜግነት ያላት አልሱ ኩርማሼቫ ለቤተሰብ ጉዳይ ነበር ባለፈው ግንቦት ወደ ሩሲያ ያቀናቸው። አልሱ ኩርማሼቫ ከባለቤቷና ከሁለት ሴት ልጆቿ ጋራ በፕራግ ነዋሪ ስትሆን፣ ጥፋተኛ ከተባለች እስከ 10 ዓመት እስር ሊፈረድባት እንደሚችል ቀጣሪ ድርጅቷ ማስታወቁን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG