በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በጥቁር ባሕር ላይ የሚበሩት የአሜሪካ ድሮኖች የቀጥታ ግጭት መንስዔ ሊሆኑ ይችላሉ” - ሩሲያ


MQ-9 ሰው አልባ ሰው አልባ አውሮፕላኖች
MQ-9 ሰው አልባ ሰው አልባ አውሮፕላኖች

አሜሪካ በጥቁር ባሕር ላይ የምታበራቸው ድሮኖች የቀጥታ ወታደራዊ ግጭት መንስዔ ሊሆኑ እንደሚችሉ ሩሲያ ዛሬ ዓርብ አስጠንቅቃለች፡፡ ሩሲያ ማስጠንቀቂያውን ያወጣችው በክሪሚያ ላይ ለተፈጸመ የሚሳኤል ጥቃት ዋሽንግተንን ተጠያቂ ባደረገች በቀናት ውስጥ ነው።

ሩሲያ ወደ ግዛቷ በቀላቀለቻት ክሪሚያ የሚገኘውን የሴቫስቶፖል ወደብ ዩክሬን ባለፈው እሁድ ማጥቃቷን ተከትሎ፣ ጥቃቱ የተፈጸመው ከአሜሪካ በተገኘና የክላስተር ቦምቦችን በያዘ ሚሳዬል ነው ስትል ሩሲያ በቁጣ ክሷን አሰምታለች፡፡

በጥቃቱ ሁለት ሕፃናትን ጨምሮ አራት ሰዎች ተገድለዋል።

ክሪሚያን በሚያካልለው የጥቁር ባሕር ላይ የአሜሪካ ሰው አልባ በራሪ አውሮፕላኖች በተደጋጋሚ እየታዩ ናቸው ሲል የሩሲያው የመከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ዓርብ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ድሮኖቹ የቅኝት ስራ እየሰሩ መሆናቸውንና ዩክሬን የሩሲያ ዒላማዎችን ለመምታት የሚያስችላትን መረጃዎች እየሰበሰቡ እንደሆነም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጨምሮ ገልጿል።

እንዲህ ዓይነት በረራዎች የቀጥታ ወታደራዊ ግጭት ስጋት ሊሆኑ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አስጠንቅቋል።

አሜሪካ በጥቁር ባሕር ላይ የድሮን በረራዎችን የምታደርግ ሲሆን፣ ይህም የማንም ግዛት ባልሆነ ክልልና በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት የሚደረግ መሆኑ ትገልጻለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG