በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ዩክሬንን በሚሳየል እና በድሮኖች አጠቃች


ሩሲያ በዩክሬን የኻርኪቭ ግዛት ያደረሰችው የሚሳይል ጥቃት
ሩሲያ በዩክሬን የኻርኪቭ ግዛት ያደረሰችው የሚሳይል ጥቃት

ሩሲያ፣ ዛሬ ሰኞ በፈጸመችው ጥቃት ሁለት ሕፃናት እና ነፍሰ ጡር ሴትን ጨምሮ፣ ስድስት ሰዎች መቁሰላቸውን በዩክሬን የኻርኪቭ ግዛት አገረ ገዥ ተናገሩ፡፡

አገረ ገዥው ኦሌ ሲነኹቦይ፣ በመኖሪያ ቤት ሕንፃዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚያሳይ ቪዲዮ፣ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አውጥተዋል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው፥ ኢስካንደር ተብሎ በሚጠራው ሚሳየል እንደኾነ፣ አገረ ገዥው ተናግረዋል፡፡

ዛሬ ሰኞ ማለዳው ላይ፣ የዩክሬን ጦር ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ቃል አቀባይ አርካዲ ኮቫሌ፣ ሩሲያ፥ 40 የክሩዝ ሚሳየሎች ወደ ዩክሬን መተኮሷን ገልጸዋል፡፡

በካስፔን የባሕር ግዛት ከሚገኝ የሩሲያ የጦር አውሮፕላን ከተተኮሱት ውስጥ፣ 37 ኬኤች 101 እና ኬኤች 555 የተባሉ ክሩዝ ሚሳየሎች፣ በዩክሬን መከላከያ መምከናቸውን ኮቫሌ ተናግረዋል፡፡ 29 ኢራን ሠራሽ ድሮኖች መደምሰሳቸውንም ኮቫሌ አስታውቀዋል፡፡

ለአምስት ሰዓታት የዘለቀው ጥቃት እኩለ ሌሊት ላይ ሲጀምር፣ ወታደራዊ ተቋማት እና ወሳኝ የመሠረተ ልማት አውታሮች፣ የምት ዒላማ መደረጋቸውን፣ የዩክሬን ባለሥልጣናት ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG