በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በገና ዕለት የዩክሬንን የኃይል መሠረተ ልማቶች መታች


የዩክሬን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የሩሲያ የሚሳዬል ጥቃት ተከትሎ የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ ሲያጠፉ፤ በዲኒፕሮፔትሮቭስክ፣ ዩክሬን፣ እአአ ረቡዕ ታኅሣሥ 25/2024
የዩክሬን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የሩሲያ የሚሳዬል ጥቃት ተከትሎ የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ ሲያጠፉ፤ በዲኒፕሮፔትሮቭስክ፣ ዩክሬን፣ እአአ ረቡዕ ታኅሣሥ 25/2024

ሩሲያ በዩክሬን የነዳጅ እና ሌሎችም የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ተከታታይ የሚሳዬል ጥቃት መፈጸሟንና በርካቶች በዛሬው ገና ዕለት ካለ ኤሌክቲሪክ ኅይል መቅረታቸውን የዩክሬን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

በጥቃቱ 78 የአየር እና የምድር ተወንጫፊ ሚሳዬሎች እንዲሁም 106 ሻሂድ እና ሌሎች ዓይነት ድሮኖች ጥቅም ላይ መዋላቸው ታውቋል። በርካታ ዩክሬናውን በገና ዕለት በምድር ውስጥ የባቡር ጣቢያዎች ለመጠለል ተገደዋል። በጥቃቱ ቢያንስ አንድ ሰው ሳይሞት እንዳልቅረ ተነግሯል።

በተለይም በካርኪቭ ክልል በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በቀዝቃዛው ወቅት ሙቀት ማግኘት እንዳልቻሉም ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል ሩሲያ ውስጥ አንድ ድሮን በአየር ላይ ተመቶ ፍርስራሹ ሲወድቅ የአንዲት ሴትን ሕይወት ሲያጠፋ ሦስት ሰዎች ደግሞ ተጎድተዋል።

“ፑቲን ሆን ብለው በገና ዕለት ጥቃቱን ፈጽመዋል። ከዚህ በላይ ኢሰብአዊነት አለን?” ሲሉ የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ በ X ማኅበራዊ መድረክ ላይ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። “ሩሲያ በመላው ዩክሬን ኅይል እንዲቋረጥ በማጥቃት ላይ ነች” ሲሉም አክለዋል።

አንድ ሚሳዬል የሞልዶቫንና የሮማንያን የአየር ክልል አልፎ እንደመጣ የዩክሬኑ የውጪ ጉዳይ ምኒስትር አንድሪል ሲቢሃ አስታውቀዋል።

ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጥቃት የጀመረችው ከሁለት ዓመታት በፊት በገና ዋዜማ መሆኑ ይታወሳል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG