በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞስኮ እና ኪየቭ በዩክሬይን የኒዩክሌር ማመንጫ ጣቢያ ጉዳይ እየተወነጃጀሉ ነው


FILE - A Russian serviceman guards an area of the Zaporizhzhia Nuclear Power Station in territory under Russian military control, southeastern Ukraine, May 1, 2022.
FILE - A Russian serviceman guards an area of the Zaporizhzhia Nuclear Power Station in territory under Russian military control, southeastern Ukraine, May 1, 2022.

ሩሲያ እና ዩክሬን ከኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያው አቅራቢያ ለተፈጸሙ ተኩሶች ትላንት አርብ በድጋሚ አንዱ ሌላውን መወንጀላቸውን በቀጠሉበት ባለሞያዎች ከኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ተገኝተው ጣቢያው መመርመር የሚችሉበት እድል በአስቸኳይ እንዲፈጠር ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥሪ አቅርቧል።

የዩክሬን ባለስልጣናት የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ከሚገኝበት ስፍራ በቅርብ ርቀት ዲኒፐር ከተባለው ወንዝ ማዶ ካለችው የማርሃኔትስ ከተማ ላይ የሩስያ ጦር ከ40 በላይ ተወንጫፊ አረሮችን ተኩሷል” ሲሉ ከሰዋል።

በጥቃቱም አንድ የ12 ዓመት ታዳጊን ጨምሮ ሶስት ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል” ሲሉ የግዛቲቱ አገረ ገዢ ቫለንቲን ሬዝኒቼንኮ ተናግረዋል።

ሩሲያ በበኩሏ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያው ላይ በመተኮስ ዩክሬንን ትወነጅላለች።

ትላንት አርብ በኃይል ማመንጫ ጣቢያው አካባቢ ከባድ ውጊያ መካሄዱ እና የመድፍ ተኩስ ጭምር መሰማቱም ተዘግቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት IAEA ኃላፊ ውጊያው ካልቆመ እና የኒውክሌር ተቆጣጣሪዎች ወደ ጣቢያው እንዲገቡ ካልተፈቀደ በስቀር "ተጨባጭ የኒውክሌር አደጋ ስጋት መኖሩ ይቀጥላል" ብለዋል።

የአይኤኢኤ ዋና ኃላፊ ራፋኤል ግሮሲ ባለፈው ሐሙስ ተሲያት ላይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በሰነዘሩት አስተያየት “ይህ ከባድ እና አደገኛ ሰዓት ነው” ነበር ያሉት።

‘አይኤኢኤ ወደ ዛፖሪዥሂያ ተጉዞ ተልዕኮውን ማከናወን ይችል ዘንድ በአስቸኳይ ሊፈቀድለት ይገባልም’ ብለዋል።

“የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያውን የተቆጣጠሩት የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን ጦር ሰራዊት ይዞታዎች ላይ ጥቃት ለማድረስ ጣቢያውን እንደ መሸሸጊያ ጋሻ ተጠቅመውበታል” በሚል ተወንጅለዋል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ከኃይል ማመንጫ ጣቢያው አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች ከፍተኛ ድብደባ መፈጸሙም ተዘግቧል።

የሩስያ ወታደሮች ተቋሙን ቢቆጣጠሩትም ዩክሬናውያኑ የጣቢያው ሰራተኞች በተቋሙ የሚሰሩትን ሥራ መስራታቸውን ግን ቀጥለዋል።

በተናጠል ዜና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በሰጡት መግለጫ የዛፖሪዥሂያ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ “ለምንም ዓይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴ ዓላማ ጥቅም ላይ መዋል የለበትም” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

አክለውም "ከቴክኒካዊ አሰራር አንጻር የአካባቢውን ደህንነት ለማረጋገጥም የውጊያ ቀጠና ውጭ የደህንነት ጥበቃውን አስተማማኝነት የሚያረጋግጥ አስቸኳይ ስምምነት ያስፈልጋል" ብለዋል።

በሌላ ዜና የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ትላንቱ አርብ ባሰሙት ንግግር ዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎች ሃገሮች ሩሲያን በአሸባሪ መንግስትነት እንዲፈርጇት አሳስበዋል። ዘሌንስኪ ዘወትር በምሽቱ ለሕዝባቸው የሚያሰሙት የቴሌቭዥን ንግግራቸው አካል በሆነው በዚህ አስተያየታቸው “ወራሪዎች በዩክሬን ላይ ይህን ሁሉ ከፈጸሙ በኋላ የቀረው አንድ ምላሽ ‘ሩሲያን በአሸባሪ መንግስትነት መሰየም ነው’ ብለዋል።

ይህንኑ ተከትሎም አንድ ከፍተኛ የሩሲያ ባለስልጣን በትላንትናው ዕለት ሲናገሩ፦ “የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ሩሲያን በአሽባሪነት የሚፈርጅ ህግ ያጸደቀ እንደሁ፡ በሞስኮ እና በዋሽንግተን መካከል ያለው ግንኙነት ክፉኛ ይጎዳል።” ብለዋል።

የሩስያው የዜና ወኪል ታስ በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰሜን አሜሪካ ክፍል ኃላፊ አሌክሳንደር ዳርቺዬቭ’ን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ድርጊቱ “የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን ደረጃ ዝቅ የሚያደርግና ምናልባትም እስከ ማቋረጥ የሚያደርስ፣ በሁለቱም በኩል እጅግ የከፋ ጉዳት የሚያደርስ ሊሆን ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

"ሩሲያውያን ለተወሰነ ጊዜ ከዚያ መቆየታቸውን እና ከኃይል ማመንጫው አካባቢ በተለይ ተወንጫፊ አረሮችን መተኮሳቸውን እናውቃለን።” ያሉ አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣን በበኩላቸው፡ አክለውም “ያን የኒውክሌር የኃይል ማመንጫ ጣቢያውን መምታት የሚያስከትለውን ውጤት ጠንቅቀው የሚያውቁ ዩክሬናውያን ጣቢያውን ለመምታት ፍላጎት ይኖራቸዋል’ የሚል እምነት የለኝም።” ሲሉ ጣቢያው በዩክሬን ኃይሎች በራሳቸው ኢላማ ተደርጓል” የሚለውን የሩስያን ውንጀላ ውድቅ አድርገውታል።

XS
SM
MD
LG