በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ የዩክሬን ድሮን ጥቃት የነዳጅ ቃጠሎ አስነስቷል አለች


ነዋሪዎች የአየር ድብደባ ማንቂያ በሚሰሙበ ጊዜ በባቡር ጣቢያ ውስጥ ይጠለላሉ፤ ኪቭ፣ ዩክሬን እአአ ታህሣሥ 31 ቀን 2024
ነዋሪዎች የአየር ድብደባ ማንቂያ በሚሰሙበ ጊዜ በባቡር ጣቢያ ውስጥ ይጠለላሉ፤ ኪቭ፣ ዩክሬን እአአ ታህሣሥ 31 ቀን 2024

በሩሲያ ስሞልንስክ ክልል ተመትቶ የተጣለ የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ስብርባሪው የነዳጅ ተቋም ላይ በመውደቁ ቃጠሎ ማስነሳቱን የሩሲያ ባለሥልጣናት ዛሬ ማክሰኞ ተናገሩ።

የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር በስሞልንስክ ተመተው የወደቁትን 10 ድሮኖች ጨምሮ በአጠቃላይ 68 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡

በብራያንስክ፣ ክሬሚያ፣ ክራስኖዶር፣ ቴቨር፣ ሮስቶቭ፣ ኩርስክ እና ካልጋ ክልሎች ውስጥ የተሰማሩ ድሮኖች መምከናቸውንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

“በጥቃቱ ሌላ ምንም ዐይነት ጉዳት እና ውድመት አልደረሰም” ሲልም ሚኒስቴሩ አክሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በኪቭ እና ሱሚ ክልሎች ላይ ያነጣጠረ የሩሲያ የሚሳይል ጥቃት መፈጸሙን የዩክሬን ባለሥልጣናት ዛሬ ማክሰኞ ተናግረዋል።

የዩክሬን ጦር፣ ሩሲያ በአንድ ሌሊት ከተኮሰቻቸው 21 ሚሳይሎች ውስጥ ስድስቱን መትቶ መጣሉን እና፣ ከ40 የሩስያ ድሮኖች 16ቱን ማውደሙን አስታውቋል።

የኪቭ ከተማ ወታደራዊ አስተዳደር ኃላፊ የሆኑት ሰርሂ ፖፕኮ "ከተመቱት ሚሳይሎች የወዳደቁ ፍርስራሾች ዩክሬን ዋና ከተማ በሚገኙ ሶስት ሕንፃዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል" ብለዋል።

በሰሜን ምስራቅ ዩክሬን በሚገኘው ሱሚ ክልል፣ የተፈጸመው የሚሳይል ጥቃት “በሾስትካ ከተማ የመሠረተ ልማት ቦታዎች ላይ ያነጣጠረ ነው” ሲሉም ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG