ሩሲያ ከመቶ በላይ የሚሆኑ ድሮኖችን ወደ ዩክሬን ማምሻውን ማስወንጨፏን የዩክሬን ሠራዊት አስታውቋል።
ስድሳ ስድስት የሚሆኑትን ድሮኖች መትቶ መጣሉንም የዩክሬን ሠራዊት ጨምሮ አስታውቋል።
የኬርሶን አገረ ገዥ በቴሌግራም እንዳስታወቁት፣ የሩሲያ ጥቃት አንድ የመኖሪያ ሕንጻን መትቶ ሁለት ሰዎችን ገድሏል። ከንቲባው በበኩላቸው 13 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን አስታውቀዋል።
የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ዛሬ ሰኞ ባወጣው መግለጫ፣ 21 የዩክሬን ድሮኖችን ማውደሙን ገልጿል። ድሮኖቹ ሁለት የንግድ ሱቆች ላይ ጉዳት ሲያደርሱ፣ ሁለት ሰዎችም ተጎድተዋል ተብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዩክሬን ትላንት እሁድ በምድር ለመፈጸም የሞከረችውን ድንበር ዘለል ጥቃት ማክሸፏን ሩሲያ አስታውቃለች፡፡
በብራይንስክ ድንበር በኩል የተሞከረው ጥቃት መቀልበሱንና ዩክሬናውያኑም ተመተው መመለሳቸውን የአካባቢው አገር ገዥ አስታውቀዋል።
ወሬውን በተመለከተ የዩክሬን ባለስልጣናት አስተያየት እንዳልሰጡ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።
መድረክ / ፎረም