በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በኪቭ ከዜለነስኪ ጋር ተገናኙ

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ጋር ዛሬ አርብ ኪቭ ውስጥ ተገናኝተዋል፡፡
የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ጋር ዛሬ አርብ ኪቭ ውስጥ ተገናኝተዋል፡፡

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ጋር ዛሬ አርብ ኪቭ ውስጥ ተገናኝተዋል፡፡

ሞዲ ከዜለነስኪ ጋር የተገናኙት በሞስኮ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ከተገናኙ ሳምንታት በኋላ ነው፡፡

ዩክሬን ከሶቭየት ህብረት ከተለየች እኤአ ከ1991 በኋላ አንድ የህንድ መሪ ዩክሬንን ሲጎበኝ ሞዲ የመጀመሪያው ናቸው፡፡

ዜለነስኪ ሞዲ በዚህ ወር መግቢያ ላይ በሞስኮ ባደረጉት ጉብኝት አዝነው እንደነበር ተመልክቷል፡፡

ሞዲ ከውይይታቸው በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት የጋራ መግለጫ ወደ ኪቭ የመጡት የሰላም መልእክት ይዘው መሆኑን ገልፀው በተገኘው አጋጣሚ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ውይይት እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ህንድ ለሰላም በሚደረገው ማንኛውም ጥረት ውስጥ ንቁ ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆኗን የገለጹት ሞዲ ግጭቱን ለመፍታት የውይይት እና የዲፕሎማሲን አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተዋል።

ምንም እንኳ የሞዲው የሀምሌው የሩሲያ ጉብኘት በአምስት ዓመት ውስጥ የተደረገ ቢሆንም ህንድ እና ሩሲያ የረዥም ጊዜ ግንኙነት አላቸው፡፡ እኤአ ከ 2000 ጀምሮም ዓመታዊ ጉባኤያቸውን ሲያካሂዱ ቆይተዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG