የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ቦሪስ ፒስቶሪየስ ከሦስት ዓመታት በፊት በሩሲያ የተከፈተባትን ወረራ ለመመከት የምትዋጋውን ዩክሬንን ዛሬ ማክሰኞ ጎብኝተዋል፡፡
የጀርመኑ የመከላከያ ሚኒስትር ዩክሬንን የጎበኙት ከተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በዓለ ሲመት አንድ ሳምንት በፊት ሲሆን በአዲሱ አስተዳደር የዩክሬን ፖሊሲ ለውጥ ሊለወጥ ይችላል የሚሉ ጥያቀዎች እየተነሱ ባሉበት በዚህ ወቅት መሆኑ ነው፡፡
የጉብኝቱ ዓላማ ለዩክሬን የሚደረገው ድጋፍ የሚቀጥል መሆኑን ለማረጋገጥ መሆኑን የጀርመን ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ የሩሲያ ክልሎች ባለሥልጣናት አካባቢዎቻቸው በዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት እንደደረሰባቸው ዛሬ ማክሰኞ ተናግረዋል፡፡ ጥቃት ከደረሰባቸው መካከል የሩሲያ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች የጦር ሠፈር ይገኝበታል፡፡
ባለፈው ሳምንትም የዩክሬን ጦር ለጦር ሠፈሩ ነዳጅ የሚያቀርበውን የነዳጅ ማጠራቀሚያ አጥቅቷል፡፡
የሩሲያ ጦር በ11 የተለያዩ ክልሎች የሩስያ ጦር ጥቃት ለማድረስ ከተጠቀመባቸው 80 ሰው አልባ አውሮፕላኖች ውስጥ 58ቱን ማውደሙን የዩክሬን ጦር ዛሬ አስታውቋል።
መድረክ / ፎረም