በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ሃይፐር ሶኒክ ሚሳዬሏን ለሙከራ እንደማትተኩስ አስታውቃለች

ከቻይናና ከደቡብ አፍሪካ ጋር በምታደርገው የባህር ላይ ልምምድ ሃይፐር ሶኒክ ሚሳዬሏን ለሙከራ እንደማትተኩስ ሩሲያ አስታውቃለች፡፡
ከቻይናና ከደቡብ አፍሪካ ጋር በምታደርገው የባህር ላይ ልምምድ ሃይፐር ሶኒክ ሚሳዬሏን ለሙከራ እንደማትተኩስ ሩሲያ አስታውቃለች፡፡

ከቻይናና ከደቡብ አፍሪካ ጋር በምታደርገው የባህር ላይ ልምምድ ሃይፐር ሶኒክ ሚሳዬሏን ለሙከራ እንደማትተኩስ ሩሲያ አስታውቃለች፡፡

የሩሲያ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ከዚህ ቀደም አገሪቱ ሚሳዬሉን ለሙከራ እንደምትተኩስ ገልጸው ነበር።

ለ10 ቀናት በሚካሄደው የባህር ላይ ልምምድ ወቅት ዚርኮን የተሰኙት ሱፐርሶኒክ ሚሳዬሎችን ሩሲያ ለሙከራ እንደማትተኩስ ኦሌግ ግላድኪ የተባሉ ከፍተኛ የሩሲያ የባህር ኃይል ባለሥልጣን መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

“በምናደረገው ልምምድ ውስጥ ምንም ሚስጥር የለም” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

“ሞሲ 2” ብለው በሰየሙት ልምምድ ከሚሳተፉት በርካታ መርከቦች መካከል ‘አድሚራል ጎርሽኮቭ’ የተሰኘው የሩሲያ መሣሪያ ተሸካሚ መርከብ እንደሚገኝበት ታውቋል።

በኬፕታውን ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ዩክሬናውያን መልህቁን ወደጣለው የሩሲያ የጦር መርከብ ጀልባቸውን በማስጠጋት ባለፈው ሳምንት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡

ልምምዱን በማድረጓ “ደቡብ አፍሪካ በዩክሬን ላይ የተፈጸመውን ወረራና ጦርነት እንደምትደግፍ የቆጠራል” የሚል ነቀፌታ ከየአቅጣጫው በመሰማት ላይ ነው።

ደቡብ አፍሪካ ገለልተኛ መሆንን በመምረጥ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችውን ወረራ ከማውገዝ ተቆጥባለች፤ ጦርነቱ በንግግር እንዲፈታም ጠይቃለች።

XS
SM
MD
LG