በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያው ኖርጎልድ የወርቅ ማዕድን ኩባኒያ ከቡርኪና ፋሶ ሊወጣ ነው


ወጣቱ የማዕድን ቆፋሪ የወርቅ ማዕድን ማውጫ አካባቢ በሥራ ላይ በቡዳ፣ ቡርኪናፋሶ፣ የካቲት 23/2020
ወጣቱ የማዕድን ቆፋሪ የወርቅ ማዕድን ማውጫ አካባቢ በሥራ ላይ በቡዳ፣ ቡርኪናፋሶ፣ የካቲት 23/2020

የሩሲያው የወርቅ ማዕድን ኩባኒያ ኖርድጎልድ የቡርኪና ፋሶ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ሥምሪቱን እንደሚያቆም አስታወቀ። ትናንት ባወጣው መግለጫ ከውሳኔው ላይ የደረሰው የሃገሪቱ ጸጥታ መደፍረስ እየተባባሰ በመሄዱ ነው ብሏል።

ቡርኪና ፋሶ እንደ አጎራባቾችዋ ማሊና ኒዠር ሁሉ ከአልቃይዳ እና ከአይኤስ ጋር ግንኙነት ካላቸው ታጣቂዎች ጋር በመፋለም ላይ የምትገኝ ሀገር ስትሆን ታጣቂዎቹ በምዕራብ አፍሪካ ሳህል አካባቢ ብዙ ሽህ ሰው ገድለዋል ከሁለት ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።

ከሩሲያው ኖርጎልድ ጋር የሚሰራው ታፓርኮ ኩባኒያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ባወጡት መግለጫ እርምጃውን የወሰድነው በማዕድን ቁፋሮ እንቅስቃሴአችን እና በሰራተኞቻችን ደህንነት ላይ የተደቀነው አደጋ እየተባባሰ በመሆኑ ነው ብለዋል።

በኩባኒያው አስር ከመቶ ድርሻ ያለው የቡርኪና መንግሥት አስተያየት እንዳላገኘ ሮይተርስ ገልጿል።

XS
SM
MD
LG