በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ለአውሮፓ ጋዝ መቅዳት እንደገና ቀጠለች


የኦፒኤል ጋዝ ማስተላለፊያ ጣቢያ በሉብሚን፣ ጀርመን እአአ ሐምሌ 21/2022
የኦፒኤል ጋዝ ማስተላለፊያ ጣቢያ በሉብሚን፣ ጀርመን እአአ ሐምሌ 21/2022

ሩሲያ በኖርድ ስትሪም የጋዝ ማስተላለፊያ ወደ አውሮፓ የምትልከውን የተፈጥሮ ጋዝ ዛሬ እንደገና ጀመረች።

መሥመሩ ላለፉት አሥር ቀናት በጥገና አገልግሎት አቋርጦ መቆየቱ ተነግሯል።

የጋዙ ፍሰት ሳይቋረጥ በፊት ወደ ነበረበት የአቅሙ 40 ከመቶ አቅርቦት ተመልሶ መድረሱን የጀርመን የኢነርጂ ተቆጣጣሪ ክላውስ ሙለር ባወጡት ትዊት አስታውቀዋል።

አቅርቦቱ የቀነሰው ካናዳ ውስጥ ጥገና ላይ የነበረው መግፊያ መሣሪያ ስላልደረሰው መሆኑን የሩሲያው መንግሥታዊ ተቋም ጋዝፕሮም ገልጿል።

ጋዝፕሮም የአቅርቦት ግዴታውን እንደሚወጣ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ገልፀው በዚህ ወር መጨረሻ ሌላኛው ተርባይን ለጥገና ሲቆም ፍሰቱ እንደገና ሊቀነስ እንደሚችል አሳስበዋል።

ምዕራባዊያን በዩክሬን ወረራ ምክንያት ለሚያሳድሩባት ጫና ምላሽ ለመስጠት ሩሲያ የነዳጅ አቅርቦቱን ልትቆርጥ እንደምትችል የአውሮፓ ኅብረት መሪዎች አስጠንቅቀዋል።

አባል አገሮቹ የጋዝ አጠቃቀማቸውን እንዲቀንሱና ሌሎች አማራጮችን እየተጠቀሙ ያላቸውን ክምችት ለመጭው ክምችት እንዲቆጥቡ የአውሮፓ ኅብረት ጠይቋል።

XS
SM
MD
LG