ዩክሬን በሁለት የሩሲያ ግዛቶች የአየር ድብደባ መፈጸሟን የሩሲያ ባለሥልጣናት ተናገሩ። በሩሲያዋ የድንበር ከተማ ቤልጎሮድ ላይ እያየለ የመጣውን የዩክሬን ጥቃት የሚመክት ‘የአጻፋ እርምጃ እወስዳለሁ’ ሲል የክሬምሊን ቤተ መንግሥት አስታወቀ።
የሩሲያ አየር መከላከያ በከተማዋ ላይ የተነጣጠሩ የሚሳኤል እና የሰው አልባ አውሮፕላኖች መትቶ በጣለበት ወቅት ሦስት ሰዎች በፍርስራሹ መቁሰላቸውን የቤልጎሮድ ግዛት አስተዳዳሪ ቭያቼስላቭ ግላድኮቭ በዛሬው ዕለት አስታወቁ። ግላድኮቭ አክለውም በበርካታ መንደሮች ያሉ የመኖሪያ ቤቶች እና ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት ደርሷል’ ብለዋል።
የዩክሬኑ የአየር ድብደባ ዜና የተሰማው የሩሲያ አየር መከላከያ በቤልጎሮድ ላይ የታለሙ 10 ኢላማዎችን ካወደሙ ከአንድ ቀን በኋላ ነው። አካባቢው ባለፉት ሳምንታት የዩክሬን ጥቃቶች ኢላማ ሲሆን፣ ባለፈው ወር መገባደጃ ላይ በተካሄደው የሚሳኤል እና የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት 5 ህጻናትን ጨምሮ 25 ንፁሀን ዜጎች መገደላቸው ተዘግቧል።
በዋናነት በዩክሬን መከላከያ ኢንዱስትሪ የታለሙ ጥቃቶች ለመፈጸም የሚያስችሏትን የክሩዝ ሚሳኤሎች በማከማቸት ላይ ናት’
በሌላ ዜና በምዕራብ ሩሲያይቱ የኦርዮል ግዛት በዛሬው ዕለት ሁለት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ኦሪዮል ከተማ ውስጥ የሚገኝ የነዳጅ ማደያ ላይ ባደረሱት ጥቃት ታስነሳው እሳት ኋላ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን የግዛቲቱ አገረ ገዥ አንድሬይ ክላይችኮቭ በቴሌግራም ባስተላለፍት መልዕክት አስታውቀዋል። ኦሪዮል ከዩክሬን ድንበር 220 ኪሎ ሜትሮች ርቃ የምትገኝ ከተማ ናት።
ምዕራባውያን ባለሥልጣናት እና ተንታኞች ሩሲያ ባለፈው ዓመት ይበልጡን በዩክሬን የመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ አነጣጥረው ከነበሩት የአየር ጥቃት በተቃራኒ በያዝነው የክረምት ወራት ‘በዋናነት በዩክሬን መከላከያ ኢንዱስትሪ የታለሙ ጥቃቶች ለመፈጸም የሚያስችሏትን የክሩዝ ሚሳኤሎች በማከማቸት ላይ ናት’ ሲሉ አስጠንቅቀው ነበር። ይሁንና እስካሁን የሩሲያ ጥቃቶች በአብዛኛው በተደጋጋሚ የመቱት የሲቪል አካባቢዎችን ነው።
መድረክ / ፎረም