በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ለአፍሪካ በነጻ እህል ታቀርባለች - ፑቲን


ፕሬዚዳንት ቭላድርሚር ፑቲን
ፕሬዚዳንት ቭላድርሚር ፑቲን

በጥቁር ባህር በኩል ከዩክሬን እህል የሚወጣበት ሥምምነት የማይታደስ ከሆነ፣ ሩሲያ ለአፍሪካ በነጻ እህል ታቀርባለች ሲሉ ፕሬዚዳንት ቭላድርሚር ፑቲን ትናንት አስታውቀዋል።

እህል በጥቁር ባህር ወደቦች በኩል ከዩክሬን እንዲወጣ ያስቻለውና ከሞስኮ ጋር የተደረሰው ሥምምነት የግዜ ገደብ ሊያበቃ ሲል እንደገና መታደሱን ባለሥልጣናት ማረጋገጣቸውን የአሶስዬትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል።

በዓለም አቀፍ የሩሲያና አፍሪካ የፓርላማ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ፑቲን ሥምምነቱ የተራዘመው ለ60 ቀናት ብቻ ነው ብለዋል። ሁሉም ወገኖች በሥምምነቱ ውስጥ ለተካተቱ የሩሲያ ቁልፍ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲገዝ ፑቲን ጠይቀዋል።

ከ60 ቀናት በኋላ ሥምምነቱን እንደማያድሱ የተናገሩት ፑቲን፣ ሩሲያ ወደ አፍሪካ የሚላከውን እህል በተመለከት አስፈላጊውን መጠን በነጻ እንደሚያቀርቡ አስታውቀል። ዩክሬንና ሩሲያ በዓለም የስንዴ የገብስና የሱፍ እንዲሁም ሌሎችም የምግብ ሸቀጦች ከፍተኛ አቅራቢዎች ሲሆኑ፣ ታዳጊ አገሮች በእነርሱ በሚላከው እህል ላይ ጥገኞች ናቸው።

ባለፈው ሐምሌ በቱርክና በተመድ አደራዳሪነት ከሩሲያና ዩክሬን ጋር ለ120 ቀናት የተደረሰው ሥምምነት፣ የዓለም የዳቦ ቅርጫት ከሆነችው ዩክሬን በጥቁር ባህር በኩል እህልና ማዳበሪያ እንዲወጣ አስችሏል።

የመጀመሪያው ሥምምነት ባለፈው ህዳር ለ120 ቀናት ታድሶ የነበረ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ሲታደስ ለሁለተኛ ግዜ መሆኑ ነው።

XS
SM
MD
LG