በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩስያ - የቀድሞ የሩስያ ሰላይ ጉዳይ

ዲሚትሪ ፔስኮቭ
ዲሚትሪ ፔስኮቭ

ሩስያ እስካሁን ባለው ጊዜ ያነጋገረኝ ክፍል ባይኖርም በጸና ስለታመሙት የቀድሞ የሩስያ ሰላይ ጉዳይ ከሚመረምሩት የብሪታንያ ባለልስጣኖች ጋር ለመተባበር ዝግጁ ነኝ ብላለች። ሰውየው በጠና ታመው ሆስቲፓል የገቡት ምንነቱ ላልታወቀ ንጥረ ነግር ከተጋለጡ በኋላ ነው።

ሩስያ እስካሁን ባለው ጊዜ ያነጋገረኝ ክፍል ባይኖርም በጸና ስለታመሙት የቀድሞ የሩስያ ሰላይ ጉዳይ ከሚመረምሩት የብሪታንያ ባለልስጣኖች ጋር ለመተባበር ዝግጁ ነኝ ብላለች። ሰውየው በጠና ታመው ሆስቲፓል የገቡት ምንነቱ ላልታወቀ ንጥረ ነግር ከተጋለጡ በኋላ ነው።

የብሪታንያ ሚድያ በገለጸው መሰረት ሰርገይ ስክሪፓል የተባሉት ሰው ዩናይትድ ስቴትስና ሩስያ ከስምንት አመታት በፊት ባደረጉት የሰላዮች ልውውጥ መሰረት በብሪታያ ጥገኝነት አግኝተዋል።

የክረምሊን ቤተ-መንግስት ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የሰውየው መታመም በጣም ያስዝናል ካሉ በኋላ የሩስያ መንግስት ስለጉዳዩ መረጃ እንደሌለው ጠቁመዋል።

የ66 አመት እድሜው ስክሪፓል በሰላሳዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ካለች ሴት ጋር ሆነው ባለፈው እሁድ ሳልስበሪ ከተማ በሚገኝ የገበያ መደብር ወንበር ላይ እንደተቀጡ ተዝለፍልፈው ተገኝተዋል። በአሁኑ ወቅት ሁለቱም በጠና ታመው በሆስፒታል እየታከሙ ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG