ዋሺንግተን ዲሲ —
የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን፣ ዋሺንግተን ላይ ከዩናይትድ ስቴትሱ አቻቸው ዶናልድ ትረምፕ ጋር ለመገናኘት ፈቃደኛ መሆናቸውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ አስታወቁ።
ላቭሮቭ፣ ከመንግሥታዊው ዜና አውታር ኖቪስት የዜና አገልግሎት ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣
“ፑቲን ለእንዲህ ዓይነቱ ውይይት ዝግጁ ናቸው” ብለዋል።
የምንመራው ወይም መረጃችን፣ ለማንም ግልፅ የሆነውና ፕሬዚዳንት ትረምፕ በስልክ ያስተላለፉት ግብዣ መሆኑን ያመለከቱት ላቭሮቭ፣ ከፑቲን ጋር በዋይት ኃውስ ለመገናኘት ቀጠሮ አድርገዋል ብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ