በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፑቲን ለአራተኛ ጊዜ በፕሬዚዳንትነት ለማገልገል ቃለመሃላ ፈፀሙ


የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን
የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን

የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ለአራተኛ ጊዜ በፕሬዚዳንትነት ለማገልገል ዛሬ ቃለመሃላ ፈፅማዋል። ለ 18 ዓመታት ያህል በሥልጣን የቆዩት ፑቲን የውጭ ፖሊሲው ቀጣይነት እንዲኖረውና የአሀገሪቱን ብልፅግና ለማዳበር ጥረት ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

የርሳቸው አስተዳደር የሀገሪቱን “ክብር” መልሷል ሲሉ በቃለ፡መሃላው ሥነ፡ሥርዓት ተናግረዋል።
እንደ ሀገር መሪ የሩስያ ጥንካሬና ብልግና እንዲበዛ የተቻለኝን ሁሉ አደራጋለሁ ብለዋል። “የህይወቴና የሥራዬ ዓላማ የእናት ሀገሪን ህዝብ ማገልግል ነው” በማለትም በሩስያ ፖለቲከኞችና የባህል ልሂቃን ለተሞላው የክረምሊን ቤተ፡መንግሥት አደራሽ አስገንዝበዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG