በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ 31 የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ሠራተኞች ከሃገር እንዲወጡ አዘዘች


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ሞስኮ፤ ሩሲያ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ሞስኮ፤ ሩሲያ

ሩሲያ ትናንት ረቡዕ ባሳታወቀችው ትዕዛዝ ከ3 ዓመት በላይ የቆዩ በሞስኮ የሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ሠራተኞች እኤአ ከጥር 31 ጀምሮ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ማዘዟ ተነገረ፡፡

እምርጃው ዩናይትድ ስቴትስ በሃገሯ የሚገኙ የሩሲያ ዴፕሎማቶችን የአገልግሎት ዘመን ለመገደብ ለወሰነቸው ውሳኔ አጸፋ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

ባለፈው ሳምንት በዩናይትድ ስቴትስ የሩሲያ አምባሳደር ዩናይትድ ስቴትስ 27 የሩሲያ ዲፕሎማቶችና ቤተሰቦቻቸው እኤአ እስከ ጥር 30 ቀን ድረስ ሃገር ለቀው እንዲወጡ ማዘዟን ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

በሩሲያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለው ግንኙነት ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ አንጻራዊ መረጋጋት ያሳየ ቢሆንም ሩሲያ ዩክሬን አካባቢ ወታደሯችን ማስፈር ከጀመረች ወዲህ እንደገና መካረሩ እየታየ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG