በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ኔቶ ወታደሮቹን ወደ ዩክሬን የሚልክ ከሆነ እጅግ አደገኛ ሁኔት ይፈጠራል” ሩሲያ


የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ወታደሮችን ወደ ዩክሬን የሚልክ ከሆነ “እጅግ አደገኛ” ሊሆን እንደሚችል ሩሲያ ዛሬ ረቡዕ አስጠንቅቃለች፡፡ የኔቶ ወታደሮች ጣልቃ እንዲገቡ ዩክሬን ያቀረበችውን ጥያቄ ሞስኮ በቅርበት እየተከታተለች መሆኑንም አስታውቃለች።

በዩክሬኑ ፕሬዝደንት ድህረ ገጽ ላይ የተለጠፈው የአቤቱታ ደብዳቤ፤ ዩክሬን አሜሪካን፣ እንግሊዝን እና ሌሎች ሃገራትን፣ የሩሲያን ወረራ ለመቀልበስ ወታደሮች እንዲልኩ መጠየቅ እንዳለባት አመልክቷል።

“በኪቭ የሚገኘው አገዛዝ ለግምት አይመችም” ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ በዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል።

የኔቶ ሃገራት ወታደሮች በምድር ላይ ባለው ውጊያ ጣልቃ የሚገቡ ከሆነ፣ ከባድ አደጋ ሊያስከትል ይችላል”

“የኔቶ ሃገራት ወታደሮች በምድር ላይ ባለው ውጊያ ጣልቃ የሚገቡ ከሆነ፣ ከባድ አደጋ ሊያስከትል ይችላል” ሲሉም አክለዋል ፔስኮቭ።

የአቤቱታ ደብዳቤው ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንኪ በመቀበልም ሆነ ውድቅ በማድረግ ምላሽ እንዲሰጡበት የሚያስፈልገውን 25ሺሕ ድምፅ ያገኝ እንደሆነ እስከ አሁን ግልፅ አይደለም። ደብዳቤው እስከ ዛሬ ረቡዕ 1ሺሕ 549 ድምፅ አግኝቷል።

ኔቶ እስከ አሁን ከባድ መሣሪያዎችን ለዩክሬን በማቀበል እገዛ በማድረግ ላይ ሲሆን፣ በቀጥታ ወታደሮችን በማሰማራት አልተሳተፈም። ወታደሮች የሚላኩ ከሆነ ወደ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ሊያመራ እንደሚችል የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደንም እንዲሁም የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን አስጠንቅቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG