በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ላቭሮቭ ሰሜን ኮሪያን ጎበኙ


የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ፣ ከሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋራ በፒዩንግያንግ፣ ሰሜን ኮርያ እአአ ጥቅምት 19/2023
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ፣ ከሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋራ በፒዩንግያንግ፣ ሰሜን ኮርያ እአአ ጥቅምት 19/2023

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ፣ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋራ በፒዩንግያንግ እንደተገናኙ፣ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

“በአሜሪካ የሚመራው የምዕራቡ ዓለም ካምፕ፣ የጠላትነት እና ተንኳሽ ባሕርይ አለው፤” በሚል፣ ሁለቱ ሀገራት መቀራረባቸውን የበለጠ እያጠናከሩ እንደኾነ ተዘግቧል።

ትላንት ረቡዕ ፒዩንግያንግ የደረሱት ላቭሮቭ፣ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የወሰደችውን ወታደራዊ ርምጃ ሰሜን ኮሪያ መደገፏን አድንቀዋል። መስኮብ፣ ለሰሜን ኮሪያው መሪ “ሙሉ ድጋፍ እና አንድነት” እንዳላት ላቭሮቭ መግለጻቸው ታውቋል።

የላቭሮቭ ጉብኝት፣ ከዓለም ፖለቲካ ከተገለለችው ሰሜን ኮሪያ ጋራ ያላቸውን ትብብር ያጠናከሩት ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለሚያደርጉት ጉብኝት ኹኔታዎችን እንደሚያመቻች ተመልክቷል።

ሰሜን ኮሪያ፥ “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” ብላ ለምትጠራው የዩክሬን ወረራ፣ የማያወላውል ድጋፏን በመስጠቷ፣ ሩሲያ ትልቅ ግምት እንደምትሰጠው፣ ላቭሮቭ አስታውቀዋል፡፡ በተመሳሳይ አገራቸውም፣ ለሰሜን ኮሩያ ድጋፍ እና አንድነት እንዳላት መግለጻቸውም ተጠቁሟል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG