በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ከቻይናና ከሌሎች አገራት ጋር የጦር ልምምድ ጀመረች

ሩሲያ የቻይና ኃይሎችንና ሌሎች አገሮችን ያሳተፈ ለሳምንታት የሚቆይ የጦር ልምምድ ዛሬ ሀሙስ መጀመሯ ተነገረ፡፡
ሩሲያ የቻይና ኃይሎችንና ሌሎች አገሮችን ያሳተፈ ለሳምንታት የሚቆይ የጦር ልምምድ ዛሬ ሀሙስ መጀመሯ ተነገረ፡፡

ሩሲያ የቻይና ኃይሎችንና ሌሎች አገሮችን ያሳተፈ ለሳምንታት የሚቆይ የጦር ልምምድ ዛሬ ሀሙስ መጀመሯ ተነገረ፡፡

ልምምዱ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ፍጥጫ ውስጥ የገቡት ሞስኮና ቤጂንግ እየተጠናከረ የመጣውን የጋራ መከላከል ትብብራቸውን ለማሳየት እንደሆነም የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

የጦር ልምምዱ ዓላማ፣ ሞስኮ ወታደሮችዋ በዩክሬን ጦርነት እየተሳተፉም፣ ለግዙፉ ወታደራዊ ልምምድ በቂ ጦር ያላት መሆኑን ለማሳየት እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል ፡፡

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቮስቶክ 2022 (ኢስት 2022) የተባለው የጦር ልምምድ እስከ ጳጉሜ ሁለት ድረስ የሚካሄድ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በጦር ልምምዱ ከ50 ሺ በላይ ወታደሮች፣ ከ5ሺ በላይ የጦር መሳሪያዎች፣ 140 የጦር አውሮፕላኖችና 60 የጦር መርከቦች እንደሚሳተፉበት ተገልጿል፡፡

የሩሲያው ከፍተኛ የጦር አዛዥ ጀኔራል ቫለሪ ጌራሲሞቭ ልምድዱን በአካል ተገኝተው የሚቆጣጠሩት ሲሆን፣ በርካታ የቀድሞ የሶቭየት ህብረት አገሮችን ጨምሮ ከቻይና፣ ህንድ፣ ላኦስ፣ ሞንጎሊያ፣ ኒካራጉዋና ሶሪያ፣ የተውጣጡ ወታደሮች እንደሚሳተፉበት በዘገባው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG