በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩስያ ፍትህ ሚኒስቴር ዘጠኝ መገናኛ ብዙሃንን “ለባዕዳን የሚሰሩ ወኪሎች” ብሎ ፈረጀ

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን

የሩስያ የፍትህ ሚኒስቴር የአሜሪካ ድምፅን ጨምሮ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ወጪ የሚካሄዱ ዘጠኝ የመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶችን “ለባዕዳን የሚሰሩ ወኪሎች” ብሎ ፈረጀ። እርምጃው ተቋማቱ ሩስያ ውስጥ የሚያደርጉትን ዜና የማጠናቀር እንቅስቃሴ ያወሳስባል።

የሩስያ የፍትህ ሚኒስቴር የአሜሪካ ድምፅን ጨምሮ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ወጪ የሚካሄዱ ዘጠኝ የመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶችን “ለባዕዳን የሚሰሩ ወኪሎች” ብሎ ፈረጀ። እርምጃው ተቋማቱ ሩስያ ውስጥ የሚያደርጉትን ዜና የማጠናቀር እንቅስቃሴ ያወሳስባል።

የሩስያው የፍርድ ሚኒስቴር ባለፈው ወር ባስጠነቀቀው መሰረት

‘Rado Free Europe / Radio Liberty’ የተባለውን ስርጭትና ተቀባይ አሰራጭ ጣቢያዎቻቸውንም በባዕዳን ወኪል ዝርዝር ውስጥ ከቷቸዋል።

ሩስያ የወሰደችው ይህ እርምጃ የዩናይትድ ስቴትስ የዜና ማሰራጫዎቹን ሞስኮ እኤአ በ2012 በባዕዳን ገንዘብ በሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በተመለከተ በደነገገችው ህግ መሰረት እንዲተዳደሩ ግዴታ ያስገድዳቸዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ በሩስያ እርምጃ ላይ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሄዘር ኖወርት በቅርቡ ሲናገሩ “የፍትህ ሚኒስተሩ የዜና ማሰራጫዎችን እንደባዕዳን ወኪል እንዲፈርጅ እና የኢንተርኔት እንቅስቃሴዎቻቸውን እንዲግደብና እንዲቆጣጠር የፈቀደው አዲሱ የሩስያ ህግ በሀገሪቱ የሚዲያ ነፃነት ላይ የተሰነዘረ ተጨማሪ ጥቃት ነውማለታቸው ይታወሳል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG